| Weight | 112 g |
|---|

አድ-ዱዓኡል ሙስተጃብ
160.00 Br
አዘጋጅ ፡ ሙሐመድ ጧሒር ዘይን
ትርጉም ፡ ሐሰን ታጁ
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት
ይዘት፡
በዱዓ ዙርያ በርካታ የተዘጋጁ መጽሐፎች አሉ፡፡ በዚህ መጽሐፍ ዉስጥም የተመረጡ ምርጥ ዱዓዎችና ዚክሮች ተካተዋል፡፡ዱዓ ዒባዳ ነው፡፡ አላህ ከዱዓ የሚኮፈሱትን ይቆጣል፡፡ ለሁሉም ነገር ዱዓ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ አላህ ዱዓ የሚያደርጉትን ይወዳልና፡፡ “አዱዓኡል ሙስተጃብ” መጽሐፍ በአቀራረቡ እጥር ምጥን ያለ ማንም በየትኛውም ቦታ በዕለቱ ሊገለገልበት በሚችል መንገድ የተዘጋጀ በመሆኑ ከራስ ሊለይ የማይገባው መጽሐፍ ነው፡፡
ከመጽሐፉ በጥቂቱ፡
የዱዓ እውነተኛ መገለጫ ከአላህ ፍፁም ከጃይ ሆኖ መገኘት፣ ከምድራዊው ኃይልና ብልሃት ሁሉ ተስፋ ቆርጦ ወይም ፀድቶ ወደርሱ መመለስ፣ የርሱን አቅምና ችሮታ ብቻ ተስፋ ማድረግ ማለት ነው፡፡ ከዱዓ ሥርዓቶች መካከል፡- ዉዱእ ማድረግ፣ እጅን ወደላይ ማንሳት፣ ወደ ቂብላ መዞር፣ በዱዓ ቁርጠኛ ሆኖ መለመን፣ ለምላሹ አለመቸኮል፣ ወሰን አለማለፍ … ይጠቀሳሉ ….
ያንብቡት
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
የእውቀት ማዕድ!!!
************




