| Weight | 131 g |
|---|

ከንጋት በፊት (ፍካሬ በነፍስ ጽዳትና በስብእና እነጻ ዙሪያ)
110.00 Br
ዝግጅት፡ ኹራም ሙራድ
ትርጉም፡ ሱለይማን ጠይብ
ይዘት፡
‹‹ከንጋት በፊት›› የተሰኘው ይህ መጽሐፍ ትኩረት ለተነፈገው ግና የአላህ ባሮች ወደ እርሱ በይበልጥ ቢቃረቡ ልመናቸው የሚሰማበትን ውዱን ሰዓታት አጽንዖት ለመስጠት ሲባል በጥንቃቄ የተመረጠ ርዕስ ነው፡፡የለሊት መገባደጃ ሰዓታት ለጥሞና እና ለመንፈሣዊ ለውጥ እጅጉን ይመቻሉ፡፡ በእነዚህ ሰዓታት ልብ ጥሞናና ትኩረት እንድትላበስና በንቃት ላይ ሆና ከሕይወት ስንክሳሮች ነጻ እንድትሆን የሚያስችል ድልብ ሀብት የምታገኝበት ወቅት ነው፡፡ መጽሐፉ በሰባት ምዕራፎች ተደራጅቷል፡፡ በምዕራፎቹ የተለያዩ ነፍስን የሚያጠሩ ሐሳቦችና ምክሮች ይቀርቡበታል፡፡ ነፍስን ስለማነጽ ሒደቶች፣አላህን ስለማስታወስ (ዚክር)፣ ወደአላህ ስለሚደረጉ የተለያዩ መቃረቢያ ስልቶች፣ ከአላህ ጋር ስለሚደረግ ግንኙነት፣ በእርሱ መንገድ ስለሚደረግ መለገስ፣ ከፍጡራን ጋር በመኗኗር ውስጥ ስለሚገኝ መቃረብና ስለመጨረሻው ጉዞ ለልብ የሚሆኑ ጣፋጭ ምክሮች(ነሲሐ) በሚገባ ተተንትኗል፡፡ መጽሐፉ አነስተኛ መጠን ስላለውም ደጋግሞ ለማንበብ ምቹ በመሆኑ ውድ አንባቢያን ቢጠቀሙበትና ለለውጥ በመነሳሳት እንዲያነቡትም ይመከራል፡፡
ያንብቡት
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
የእውቀት ማዕድ!!!
************




