| Weight | 103 g |
|---|

ሚዛናዊነት በሙስሊም ሕይወት ውስጥ
130.00 Br
ዝግጅት፡ ዶ/ር ሙሐመድ ሙሳ አሽ-ሸረፍ
ትርጉም፡ ዐብዱልከሪም ታጁ
አሳታሚ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
ስለመጽሐፉ ይዘትና ማብራሪያ፡
ዛሬ ላይ በርካታ ወገኖች ሚዛናዊ ነን ይላሉ፡፡ ይህ መጽሐፍ ስለ ሚዛናዊነት ምንነት በነገሮች ዉስጥ ሁሉ ሚዛናዊ የመሆን አስፈላጊነት፤ጠንካራ ፍላጎቶችንና የራስ ዝንባሌዎችን አመዛዝኖ ስለመያዝ፣ ሚዛናዊ ለመሆን ስለሚረዱ መንገዶች፣ ሚዛናዊነትን ለማረጋገጥ መሟላት ስለሚገባቸው ነጥቦች እና ተያያዥ ጉዳዮች የተዳሰሱበት ነው፡፡
ከመጽሐፉ በጥቂቱ:
ውስጣዊ ስሜቶቹን መግራትና በሥርዓት መምራት የቻለ ሰው ስኬታማ ይሆናል፡፡ ነፍሱ ልቅ ስሜቷን ተከትላ እንድትነጉድ እንዲሁ የለቀቃት ግን በእርግጥ ኪሳራ ላይ ይወድቃል፡፡ እንደዋለለም ይኖራል፡፡ ዛሬ፣ ኡማውን ወደ ቀድሞ የክብር ደረጃው የመመለሱ ኃላፊነት በእያንዳንዱ ሙስሊም ግለሰብ ላይ ተጥሏል፡፡ ይህን ኃላፊነቱን የሚወጣበት መንገድ ደግሞ በመጀመሪያ ራሱን ማስተካከልና ቀጥሎ ለሌሎች ጥሪ ማድረግ ነው፡፡ ነፍሱን ገርቶ፣ ራሱን መርቶ፣ በሁሉም አቅጣጫ የተስተካከለና ያማረ ስብዕና መላበስ የሁሉም ሙስሊሞች ትልቅ ግብ ቢሆንም በቀላሉ የሚሳካ ግን አይደለም፡፡ በርካታ እንቅፋቶች አሉበት፡፡ በተለይ በዚህ ዘመን ትላልቅ እንቅፋቶች ተጋርጠውበታል፡፡ …
ያንብቡት
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
የእውቀት ማዕድ!!!
************




