የደዕዋ ሰዎች ሥነምግባር

105.00 Br

አዘጋጅ፡ አቡል አዕላ አል-መውዱዲ እና ዐብደላህ ናሲሕ ዑልዋን

ትርጉም፡ ዶ/ር ኢድሪስ ሙሐመድ

አሳታሚ፡ ነጃሺ ማተሚያ  ቤት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር

 

ስለመጽሐፉ ይዘትና ማብራሪያ፡

ኢስላም ለመልካም ሥነምግባር ትልቅ ቦታ ሠጥቷል፡፡ ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) የመልካም ሥነምግባር ተምሣሌት ባይሆኑ ኖሮ ጥሪያቸው ርቆ ዓለምን ባላዳረሰ ነበር፡፡ መልካም ሥነ-ምግባር የጥልቅ እምነት አንፀባራቂና የትክክለኛ ዒባዳ ውጤት እንደሆነ ኢስላም ያስተምራል፡፡ ኢስላማዊ ሥነ-ምግባር የእምነት ነጥቦችን ከመቀበል ባሻገር ኢስላማዊውን መርህ ሕይወት ከእያንዳንዱ የሕይወት እንቅስቃሴ ጋር ለማጣጣም ጥረት ማድረግን ትዕግሥትንና ፅናትን ታማኝነትንና እውነተኝነትን ለኢስላማዊ ሥራ (ዳዕዋ) ትኩረት መስጠትንና መሰል ድንቅ ባሕሪያትን ያጠቃልላል፡፡ ይህ መጽሐፍ በሥነ-ምግባር ላይ በማተኮር የቁርኣንና የሐዲስ ማስረጃዎችን በማስደገፍ ያቀረበ ነው፡፡

 

ከመጽሐፉ በጥቂቱ:

ኢስላማዊ ሕይወትን መምራት ለደዕዋ ተግባር ስኬታማነት የሚኖረው ፋይዳ እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ ነፍሣቸዉን ማፅዳት፣ መንፈሣቸዉን ማምጠቅ በሚያደርጉት የደዕዋ እንቅስቃሴ ሌሎችን መጥቀምና የተሃድሶ ለውጥን ማምጣት ለሚሹ ሁሉ ሕይወታቸው ኢስላማዊ መሆኑ የግድ ነው፡፡ የሰናይ ምግባራት መፍለቂያ፣ የመልካም ሕይወት ጨረር መፈንጠቂያ፣ …. ኢስላማዊ ሕይወት ብቻ ነው፡፡

 

ያንብቡት

ነጃሺ ማተሚያ  ቤት

የእውቀት ማዕድ!!!

************

 

 

 

 

 

 

SKU: M015 Category: