| Weight | 75 g |
|---|
SOLD OUT

ቁርኣንን ለማንበብ
110.00 Br
አዘጋጅ ፡ ዐብዱልመናን ከበደ (አቡ ያሲር አልጊላኒ)
ይዘት፡
ቁርዓን የሙስሊሞች መመሪያ እንደሆነ እሙን ነው፡፡ የወረደዉም በዓረቢኛ ቋንቋ ነው፡፡ ይህ መመሪያ ምን መልዕክት እንደሚያስተላልፍ ለማንበብም ሆነ ለማወቅ ዓረቢኛን ማወቅ እና ፊደላቱን መለየት ያስፈልጋል፡፡የአነባብ ስልቱን ለማወቅ የዓረቢኛን ፊደላት ማወቅ ግድ ይላል፡፡ የዓረብኛ ፊደላት ከከንፈር፣ ከአፍ እና ከጎሮሮ የሚወጡ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ ፊደላት ተመሳሳይ ሆነው የመውጫ ቦታቸው ብቻ የሚለያይበት ሁኔታ አለ፡፡ ተመሳሳይ የሆኑትን ከነቅላፄያቸዉና መውጫ ቦታቸው መረዳት ይገባል፡፡ ይህ መጽሐፍ የዓረቢኛ ቋንቋ ፊደላትን፣ የፊደላቱን አነባብ፣ ቅርጽና አገባባቸዉን በዓረቢኛና በአማርኛ የሚተነትን ነው፡፡ በተጨማሪም የማጥበቂያና የማርዘሚያ፣ በግልጽ የማውጣት፣ የመጨፍለቅ፣የመደበቅና የመገልበጥ ስልቶችን በዝርዝር ያስረዳል፡፡
ከመጽሐፉ ፡
ቁርኣንን መማር ግዴታ ነው፡፡ ቁርኣንን ማንበብ መቻል የኢስላማዊ ዕውቀቶች መፈለጊያ መሠረት መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡ ቁርኣን የሕይወታችን መመርያ የፈጣሪያችን አላህ መልዕክት ነዉና፡፡ ይህ መማርያ የተለያየ መጽሐፍትን በማገናዘብና የመምህራንን ምክር መሠረት በማድረግ የተዘጋጀ ነው፡፡
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
የእውቀት ማዕድ!!!
************
Out of stock




