| Weight | 139 g |
|---|

የውመል ቂያማ
180.00 Br
ዝግጅት፡ ሃሩን ያሕያ
ትርጉም፡ ኡስታዝ አሕመድ ሑሴን (አቡ ቢላል)
ነጃሺ ማተሚያ ቤት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
ስለመጽሐፉ ይዘትና ማብራሪያ፡
በኢስላም ዉስጥ ከስድስቱ የእምነት ማዕዘናት መካከል አንዱ በመጨረሻው (የትንሳኤ ቀን ማመን ) ነው፡፡ የፍርዱ ቀን (የውመል ቂያማ) የሰውን ብቻ ሳይሆን የዚህን አጽናፈ ዓለም ሞት (መፈራረስ) የሚያስከትል ቢሆንም በሚያስደንቅ ሁኔታ አብዛኛው የዓለም ሕዝብ ፈጽሞ ሊያስበውና ሊጨነቅበት የማይፈልገው ጉዳይ መሆኑ እውነት ነው ይላል ደራሲው፡፡ ይህ የውመል ቂያማ የተሠኘው መጽሐፍ ስለዚሁ ቀን ዉሎ ቁርኣንን እንዲሁም ሳይንስን እያዛመደ ይተነትናል፡፡ የመጨረሻውን የአላህን ፍርድ ቀን አሳዛኝ የዓለም ፍጻሜን ያስቃኘናል ፡፡
ከመጽሐፉ በጥቂቱ፡
ጊዜ በአክናፎቹ ወደፊት በገሰገሰ ቁጥር የፍርዱን ቀን ወደኛ እያቀረበው መሄዱ የታወቀ ነው፡፡ ይህም ሆኖ ብዙ ሰዎች ያንን ቀን እጅግ ሩቅ እንደሆነ አድርገው ያስባሉ፡፡ የዚህች ዓለም ዕድሜ አንድ ቀን ፍፃሜ ያገኛል፡፡ የፍፃሜዋን ቀን በትክክል የሚያውቅ ዓለምን የፈጠራት ጌታ አላህ (ሱ.ወ.) ብቻ ነው፡፡ በዚህች ዓለም ላይ የኖረን ለትንሽም ሆነ ለረጅም ጊዜ የቆየ ሰው ሁሉ አላህ ፊት መቅረቡ አይቀርም፡፡ …
ያንብቡት
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
የእውቀት ማዕድ!!!
************




