የስኬት ቁልፎች

95.00 Br

ዝግጅት፡ሸይኽዶ/ርዓኢድኢብኑዐብደላህአልቀርኒ
ትርጉም፡ ዶ/ር ሙሐመድ ሰዒድ(ABX)

አሳታሚ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት ኃ/ተ/የግ/ማኅበር

 

ስለመጽሐፉ ይዘት፡

አነቃቂና አዝናኝ በሆነ መልኩ የቀረቡ ወደ ስኬት የሚያደርሱ መንገዶች፤ለሥራና ለትጋት የሚያነሳሱ አጫጭር መልዕክቶች፤ተሞክሮዎችና አስደናቂ የታዋቂ ሰዎች ታሪኮች በምሳሌነት የቀረቡበት ነው፡፡ መጽሐፉ የትልቅ ዓላማ፣ የቁርጠኛ አቋም፣ የፅኑ ፍላጎት ባለቤት እንድንሆን ያነሳሳል፡፡ በዚህም ሆነ በመጨረሻው ዓለም ወደ ስኬትና ወደ ታላቅነት መንገድ ያመላክታል፡፡ ስንፍናን እና ድካምንም ያጣጥላል፡፡ ወደ ታላላቅ ፈጠራዎችና አዳዲስ ግኝቶች እንድንወጣና ወደ ምሉእነት እንድንራመድ ይጋብዛል፡፡

 

ከመጽሐፉ በጥቂቱ፡

  • አቡበክር አስ-ስድዲቅ (ረ.ዐ) ሙሉ ሀብታቸውን በአላህ (ሱ.ወ) መንገድ ለግሰዋል፡፡
  • ዑመር ኢብኑ አል-ኸጧብን (ረ.ዐ) ሸይጧን እርሳቸው ባለፉበት አያልፍም ይሸሻቸዋል፣
  • ዑሥማን ኢብኑ ዐፍፋን (ረ.ዐ) የጭንቅ ጊዜ ሠራዊትን ትጥቅና ስንቁን ችለዋል፡፡ የመኡነህን ምንጭ በአላህ (ሱ.ወ) መንገድ ለግሰዋል፡፡ በአንዲት ረከዐህ ሙሉ ቁርአንን ያከትሙ ነበር፡፡
  • ኻሊድ ኢብኑ አል-ወሊድ (ረ.ዐ) መቶ ጦርነቶች ላይ ተሳትፈዋል፡፡ በየርሙክ ጦርነት ብቻ በሰይፋቸው አምስት ሺህ ከሀዲያንን አጭደዋል፤ በወቅቱም እጃቸው ላይ ዘጠኝ ሰይፍ ተሰባብሯል፡፡
  • ዐብዱረሕማን ኢብኑ ዐውፍ (ረ.ዐ) አንድ ሺህ ግመሎችን ከነሙሉ ሸቀጥ ጭነቶቻቸው ለድሆች ለገሱ፡፡
  • አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) አብዛኛውን የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ሐዲሦች በቃላቸው አጥንተዋል፡፡ ሌሊታቸውን ለሦስት በመክፈል ማለትም፡- ለሶላት፣ ለዲናዊ ትምህርት መማማሪያና ለእንቅልፍ በማድረግ ይጠቀሙበት ነበር፡፡አሕመድ ኢብኑ ሐንበል (ረሒመሁሏህ) ሐዲሥ ፍለጋ ሰላሳ ሺ ማይል ተጉዘዋል፡፡

 

ያንብቡት

ነጃሺ ማተሚያ  ቤት

የእውቀት ማዕድ!!!

************

 

 

 

SKU: M083 Category: