ብርቱዉ ኃይል

120.00 Br

ትርጉም፡ ዐብዱረዛቅ ነጋሽ

አሳታሚ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር

 

ከመጽሐፉ በጥቂቱ ተጋበዙልን፡

መጽሐፉ ወጣቶችን የትኩረት ማዕከል አድርጎ ነው የተፃፈው፡፡ ወጣቶች ለሚገጥማቸው ሥነ ልቦናዊ፣ ስሜታዊና አካላዊ ችግሮች መፍትሔዎችን ይጠቁማል፡፡ ስለወጣትነት የዕድገት እርከኖች፤ወጣቶች በእስልምና ውስጥ ሊኖራቸው ስለሚገባ ሚና፤ስለ ዋና ዋና መሠረታዊ ችግሮቻቸውና ሌሎችም ይዳስሳል፡፡ መጽሐፉ ወጣቶች ላይ የሚነሱ መሠረታዊ ችግሮችን በመተንተን፣ እንዴት መታከም እንደሚቻል፣ ተግባራዊ ልምምዶችን በማንሳት፣ መረጃዎችን በማጣቀስ፥ ወጣቶች ሊሆኑ የሚገባውን ባሕሪይ ያስተምራል።

 

ስለመጽሐፉ ይዘት እና ማብራሪያ፡

በሰው ልጅ ትልቁ የሕይወት ዑደት ውስጥ የወጣትነት እርከን ከልጅነት ጊዜ ጀምሮ ያለውን የለውጥ ጊዜ ወካይ ነው። ለራስም ሆነ ለሌሎች መታመን የሚገኝበት፤ተክለ ሰውነት የሚዳብርበት፤የአዕምሮ እና የስሜት መስተካከል ላይ የሚደረስበት የሕይወት ክፍል ነው። ወጣትነት ለማኅበረሰብ ዋና ሃብቱ፣ ቃል ኪዳኑና መሣሪያው፣ የወደፊት ዕጣ ፋንታውና ሥልጣኔው፣ ድልብ ሃብቱና የሁሉም ኃይል ምንጭ ነው። ማኅበረሰብ ይህን ውድ ሃብቱን በአግባቡ መጠበቅ ከቻለ እንዴት አያድግም? እንዴትስ ከፍታው እውን አይሆንም?! እንዴትስ ከነርሱ ተጠቃሚ ሆኖ መጥቀም አይችልም?! የመጣንበትን ዓላማና መልእክት በሚገባ ለማድረስ ከሞከርን ወደ ምድር የመጣንበትን ሚስጥር በማሳካት ምድርን እናለማለን። በተቃራኒው የተፈጠርንበትን ግብ የሳትን ጊዜ ዕጣ ፋንታችን ዕድለ ቢሶች መካከል ይሆናል።

 

ያንብቡት

ነጃሺ ማተሚያ  ቤት

የእውቀት ማዕድ!!!

************

 

 

 

SKU: M144 Category: