| Weight | 203 g |
|---|

የማር ጠብታ
360.00 Br
አዘጋጅ፡ ኡስታዝ ሙሐመድ ዑመር
አሳታሚ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
ስለመጽሐፉ ይዘት እና ማብራሪያ፡
መጽሐፉ የሚያተኩረው የታወቁ ሰዎችን ጥልቅ ሀሳብ እና ትርጉም ያላቸውን ጥበባዊ አባባሎችን በመተንተን ላይ ነው፡፡ ሐሳቦች የድርጊቶቻችንና የአንደበቶቻችን አንቀሳቃሾች ናቸው። የእምነቶቻችንና የስሜቶቻችን ዘሮች መብቀያም ናቸው። ምድራዊ ሕይወታችንን ብቻ ሳይሆን ዘላለማዊነታችንንም የመተለም አቅማቸው ከፍተኛ ነው። ስለዚህ በዋናው ሕይወታችን ላይ የመወሰን ጉልበት ያላቸውን ታላላቅ ሐሳቦችን መርጠን በመውሰድ ራሣችንን በማነጽ በማሳደግ ረገድ ብልህ መሆን ይኖርብናል፡፡ መጽሐፉ በብዙ የሕይወት ገጽ ላይ ያለፉ የበርካታ ሰዎችን የሕይወት ልምምድ ጨምቆ የያዘ ነው። የበርካታ ምሁራን ጥናትና ምክረ ሐሳብ በተጨማሪነት ተካቶበታል።
ከመጽሐፉ በጥቂቱ ተጋበዙልን፡
‹‹ዛሬ ብቅ ብላ የሔደችው ፀሐይ ነገ ብቅ ማለቷ ተመሳሳይ የሰዓት አቆጣጠር እንድንቆጥር ትፈቅድልናለች እንጂ ያንኑ ጊዜና ዕድል ግን ይዛልን አትመጣም።›› ጊዜ ሁሉም ነገር የሕልውና እስትንፋሱን የሚያገኝበት ነው። ያለ ጊዜ ምንም ነገር ምንም ነው። ይሁንና ሳናውቅበት የምናባክነው ቁጥር አንድ ነገር ደግሞ ጊዜ ነው። ከላይ የተመለከትናት ባለታሪካችን ስትኳትን ኖራ ነበር …..
ያንብቡት
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
የእውቀት ማዕድ!!!
************




