| Weight | 55 g |
|---|

ዉድ ስጦታ ለሚስቶች
90.00 Br
በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ለተከበረው የትዳር ሕይወት ሚስት የምትከፍላቸውን መስዋእትነትና ለውዱ ባለቤቷ ያላትን ፍቅር የምትገልጽባቸው 45 መንገዶች እንዲሁም ባሎችም ሚስቶቻቸው በምን መልኩ ፍቅራቸውን ቢገልጹላቸው እንደሚወዱ የገለጹበት መጠነኛ ጽሑፍ ተካቷል፡፡ በመጽሐፉ ዉስጥ የቀረበው ሀሳብ የአዘጋጁ ነው፡፡ መጽሐፉ ትዳርን ለማጣፈጥ ሚስቶች መወጣት ያለባቸውን ኃላፊነት ይመክራል፡፡
የገጽ ብዛት ፡ 104
ከመጽሐፉ ፡
ሚስት ለባሏ ፍቅርን ከምትገልጽባቸው መንገዶች ፡- ከዉጭ ወደቤት ሲገባ በጥሩ ፈገግታና ቃላት እቀበለዋለሁ፤ ባሌ ከኔ ጋር መውጣትና መግባት ከፈለገ የቀጠሮ ሰዓቱን እጠብቃለሁ፤ ለባሌ ያለኝ ፍቅር ለመግለጽ ድንገት ሳያስብ አነስተኛ ግብዣ አድርጌ እጠብቀዋለሁ፤ ቢያመሽ ሳልተኛ እጠብቀዋለሁ፤ ሲገባም በሰላም በመግባቱ ደስታዬን እገልፅለታለሁ፤….
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት




