| Weight | 149 g |
|---|

ታላላቅ ሙስሊም ሴቶች
240.00 Br
ኢስላም ጥንታዊ ሐይማኖት ነው፡፡ ከአባታችን አደምና ሐዋ ጀምሮ የመጡ ነቢያት በሙሉ አሃዳዊ እምነት ሲያስተምሩ የኖሩ ናቸው፡፡ ታላላቅ ሙስሊም ሴቶች ጅማሮው ከእናታችን ሐዋ ጀምሮ እስከ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዘመን ያሉ አላህን በመፍራት ለአላህ በመታዘዝና ኢሰላም ባስቀመጠው መንገድ በመመራት ስመ ጥር የሆኑትን ነው ዶ/ር ዐብዱልሐሚድ ኢልዋ ያስተዋወቁን፡፡ በመጽሐፉ 38 ታላላቅ ሴቶችን እንተዋወቃለን፡፡ መጽሐፉ በ8 ምዕራፍ የተከፈለ ሲሆን በየምዕራፎች አስፈላጊና ጠቃሚ መረጃዎች ሰፍረዋል፡፡
ትርጉም ፡ አሕመድ ሑሴን (አቡ ቢላል)
የገጽ ብዛት ፡ 156
የታተመበት ዓመት ፡ ሰኔ 2004
ከመጽሐፉ ፡ በተለያዩ ቅዱሳን መጽሐፍት እንደተነገረዉና ሲወርድ ሲዋረድ እንደመጣው ትውፊታዊ ታሪክ ሐዋ የሰብዓዊ ፍጡር ሁሉ እናት መሆናቸው ይታወቃል፡፡ የተፈጠሩት ከባለቤታቸው አባታችን አደም (ዐ.ሰ.) ግራ ጎን አጥንት ነው …
ከነቢዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ.) ሕዝቦች መካከል በአላህ ለማመን የመጀመርያዋ ሴት ሳርረህ ናት፡፡ ከዚያ በኋላ የርሣቸው ባለቤት የመሆንን ዕድል አገኘች፤ በኑሩበት ዘመናት ሁሉ በአላህ መንገድ ላይ ባዩት መከራም ጭምር ከጎናቸው ነበረች ::
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት




