
ከቁርዓን መልዕክቶች
358.00 Br
አዘጋጅ ፡ አድሀም ሸርቃዊ
ትርጉም ፡ ሙሐመድ ሰዒድ (ABX)
ይዘት፡
ይህ ዓለማቀፍ ተወዳጅኝነት ያለው መጽሐፍ ‹ረሳኢል ሚነል-ቁርኣን› ይሠኛል። መጽሐፉ የተወሰኑ የቁርአን አንቀፆችን በመምረጥ በማብራራት ላይ ያተኮረ ነው። አጫጭር ዐረፍተ ነገሮች፣ ነገርግን ትላልቅ መልእክቶችን የያዙ ሐሳቦች የታጨቁበት ነው።
ከመጽሐፉ ፡
«እነዚያ አላህ የመራቸው ናቸው፣ በመንገዳቸውም ተከተል።»(አል-አንዓም፡90) አላህ ሆይ! እኔ – በርግጥ ላንተ በሚግገባህ መልኩ አልሰገድኩም፣ዳዉድ (ዐ.ሰ.) እንደሚፆሙት ዓይነት ፆም ላንተ አልፆምኩም፣ ታምሜ የአዩብን (ዐ.ሰ.) ዓይነት ትዕግሥት አልታገስኩም፣ዩኑስ (ዐ.ሰ.) በዓሣ ነባሪ ሆድ ውስጥ ሆነው ያወደሱህን ዓይነት ውዳሴ አላወደስኩህም፣ሃይማኖቴን እንደ የሕያ (ዐ.ሰ.) አጥብቄ አልያዝኩም፣ዩሱፍ (ዐ.ሰ.) ዐይናቸውን እንደሰበሩት ሆኜ መላ አካላቴን አልተቆጣጠርኩም።ያን ሁሉ ግፍና በደል ካደረሱባቸው በኋላ “እናንተ ነፃ ናችሁ በሉ ሂዱ!” ብለው ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ጠላቶቻቸውን ይቅር እንዳሉት ዓይነት ይቅርታ ለማንም ይቅር አላልኩም።
ነገር ግን አላህ ሆይ!
እኔም እንደነርሱ ነኝ፤
እነርሱ እንደሚወዱህ ሁሉ፣
እኔም እወድሃለሁ!
ያንብቡት
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
የእውቀት ማዕድ!!!
************




