| Weight | 16 g |
|---|

አንዲት ዕለት በሙስሊም ሴት ሕይወት ዉስጥ
120.00 Br
ንጽህናን እና ክብርን መጠበቅ ብርቅ በሆነበት በዚህ ፈተና በበዛበት ዘመን ለምትኖረው ሙስሊም እህት የተፃፈች ናት መጽሐፏ፡፡ እያንዳንዷን ሙስሊሟ እህት የአላህ ቅጣት እንዳያገኛት ከልቡ ከሚጨነቅ፣ እንዲሁም ጀነትን ተስፋ ከሚያደርግላት ወንድም የተላከች መልዕክት ናት ይላል አዘጋጇ፡፡ አንዲት ሙስሊም ሴት በአንዲት ቀን ዉስጥ አላህ ዘንድ የሚያስወድዳትን ወደሱ የሚያቃርባትን ምን ምን ሥራዎች መሥራት ትችላለች፡፡ በመጽሐፏ ዉስጥ ተሰናድተዋል፡፡
አዘጋጅ ፡ ሸይኽ መሕሙድ አልመስሪ
ትርጉም ፡ ዐብዱልከሪም ታጁ
የገጽ ብዛት ፡ 84
የካቲት ፡ 2007
ከመጽሐፉ ፡ ሱብሒ ላይ እህቶቿን ወይም ሴት ልጆቿን ትጠራና በጀመዓ ትሰግዳለች፡፡ ግዴታዋን ከሰገደች በኋላ እዚያው ከመስገጃዋ ሳትነሳ ዚክር ትጀምራለች፡፡ በዚሁ ዙርያ የተነገረውን ትልቅ ምንዳ ታገኝ ዘንድ፣ ፀሐይ እስክትወጣ ድረስ ዚክሯን ትቀጥላለች፡፡ ዕለቷን በዚህ ሁኔታ ከተቀበለች በኋላ፣ ለዚህች ዓለም ጠፊ ሃብት ልቧን አትሰጥም፡፡ ምክንያቱም ይህች ዓለምና በውስጧ የያዘችው በሙሉ፣ አላህ ዘንድ የትንኝ ክንፍ ታህል ዋጋ እንደሌላቸው አስረግጣ ታውቃለች፡፡ ከዚህም በላይ፣ ልቧን ለዱንያ ባለመስጠት (በዛሂድነት) እንጅ የአላህን ፍቅር እንደማታተርፍ በጥልቅ ታምናለች፡፡
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት




