| Weight | 1244 g |
|---|

ሐያእ
175.00 Br
መነሻ ሀሳብ፡ ሸኽ ሙሐመድ ኢብኑ ሙሳ አሸሪፍ
ትርጉምና ቅንብር፡ ዶ/ር ሙሐመድ ሰዒድ(ABX)
አሳታሚ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
ከመጽሐፉ በጥቂቱ:
“ሐያእ” የሚለው ቃል ትርጉሙ እጅግ ሰፊና ጥልቅ በመሆኑ በአንድ ቃል ብቻ መግለፁ ይከብዳል፡፡ እፍረት፣ ትህትና፣ ይሉኝታ … ልንለው እንችላለን፡፡ ሐያእ ሲባል ለአንድ ወገን ማለትም ለሴት አሊያም ለወንድ ብቻ የሚያስፈልግ መልካም ሥነምግባር አይደለም፡፡ ዛሬ ላይ እየጠፉ ካሉ ድንቅ የሙስሊሙ መልካም ባህሪዎች መካከል ሐያእ አንዱ ነው፡፡ ወደዚህ መልካም ባህሪ ካልተመለስን በስተቀር የወደፊቱ ደግሞ የከፋ ይሆናል የሚል ስጋት አለ፡፡ ሐያእ ከብዙ መጥፎ ነገሮች ያቅባልና አስፈላጊነቱ አያጠያይቅም፡፡ ይህ መጽሐፍም ስለ ሐያእ ምንነት፣ አስፈላጊነት፣ ዓይነቶች፣ ትሩፋቶችና ሌሎችም ተያያዥ ጉዳዮች ይዘረዝራል፡፡ ተርጓሚው ከትርጉሙ በተጨማሪ የራሱንም ሀሳቦች ጨምሮበታል፡፡
ከመጽሐፉ በጥቂቱ፡
እውነተኛ ሐያእ አላህን (ሱ.ወ) እንድንፈራና የታዘዝንበትን ነገር በአግባቡ እንድንወጣ ያደርገናል፤ከተከለከልናቸው ነገሮች እንድንርቅም ይገፋፋናል፤ከተጠራጠርነው ነገር ራሳችንን እንድናቅብና እንድንቆጥብ ይይዘናል፡፡
ሐያእ የተሰጣት ነፍስ በርግጥ ብዙ ነገርን ተሰጠች፡፡ ሐያእ ያላት ነፍስ ኑሮዋ ሁሉ የአምላኳን ውዴታ ለማግኘት ነው፡፡ ፈጣሪዋ የማይወደውን ነገር አትሠራም፣ ጨዋ ናት ዋልጌ አይደለችም፣ እርጋታ አላት አትቸኩልም አትንቀዠቀዥም፣ ሥርዓት አላት ልቅ አይደለችም፣ ዓላማ አላት በደመነፍስ አትኖርም፡፡
ሐያእ ያላት ነፍስ ክብር ያላት ናት፡፡ በተራና በርካሽ ነገሮች አትታለልም፡፡ በመጥፎ ውሎና ቦታ ላይ አትገኝም፡፡ ለስሟ ታስባለች፡፡ ለክብሯም ትጨነቃለች፡፡ ከሌሎች ጋር በመግባባት ትኖራለች፡፡ የሌሎችን መብት ታከብራለች፡፡
ያንብቡት
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
የእውቀት ማዕድ!!!
************




