የኢስላም መሠረታዊ ግንዛቤ

2.00 $

የመፅሐፉ ይዘት ፡ ስለ እስልምና እውነታ አንዳንድ ማስረጃዎች፣ ሳይንሳዊ ተዓምራት በቅዱስ ቁርኣን፣ቁርኣን ስለ ሰው ልጅ የፅንስ ዕድገት፣ ቁርኣን ስለ ተራሮች፣ ስለ ሥነፍጥረት አመጣጥ፣ ስለ አንጎል፣ ስለ ባህሮችና ወንዞች፣ ስለ ዳመና፣ ተፈጽመው ያለፉ ቁርኣናዊ ትንቢቶች፣ በነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) የተከናወኑ ተዓምራት፣ እጅግ አስደናቂው የእስልምና ዕድገት፣ የእስልምና ፋይዳዎች፣ጠቅለል ያለ መረጃ ስለ እስልምና….
ዝግጅት ፡ አይ ኤ ኢብራሂም
ትርጉም ፡ ሐሰን ናስር ዐሊ
የገጽ ብዛት ፡ 81
ጥቂት ከመፅሐፉ፡-
ዘመናዊ የከርሰ ምድር ጥናት ሳይንሶች እንዳረጋገጡት ጋራዎች ከምድር ገጽ በታች ጥልቅ የሆኑ ስሮች ያሏቸው ከመሆናቸውም በላይ የነዚህ ሥሮች እርዝማኔ ተራሮች ከምድር ገጽ በላይ ካላቸው ከፍታ ጋር ሲወዳደር በብዙ እጥፎች ሊበልጥ ይችላል፡፡ በዚህ ሀሳብ መነሻነትም ተራሮችን ለመግለጽ እጅግ ተስማሚው ቃል ‹ችካል› የሚለው ይሆናል፡፡ ምክንያቱም ደግሞ በደንብ ተደርጎ የተተከለ ችካል ከምድር ገጽ በታች በማይታይ መልኩ ተቀብሮ የሚገኝ መሆኑ ነው፡፡
አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ይላል ‹ምድርን እንደ ምንጣፍ ጋራዎችንስ እንደ ችካል አላደረግንምን?› (አን-ነበእ ፡6-7)
ተራሮች የመሬት የላይኛው ክፍል እንዳያረገርግ በማድረግም በኩል ወሳኙን ሚና ይጫወታሉ፡፡ ‹በምድርም ዉስጥ በናንተ እንዳታረገርግ በዉስጧ ተራሮችን ጣለባት፡፡› (አን-ነሕል ፡15)
ነጃሺ የዕውቀት ማዕድ!!

Category:

Additional information

Weight 88 g