የሙስሊም ወጣቶች ኃላፊነት

2.00 $

ስለ ጊዜ ጥቅም፣ ስለ ሙስሊሙ ወጣት አጠቃላይ ኃላፊነቶች የተለያዩ ነጥቦች የተዳሰሱበት መጽሐፍ ነው፡፡ ሙስሊም ወጣቶች በሕይወት ውስጥ ሊኖራቸው የሚገባው ሚና ከሕፃናት፣ ከጐልማሶችና ከእናቶች የተለየ ነው፡፡ ወጣቶች ለእውቀት ጉጉ ናቸው፡፡ ለአንድ ነገር መስዋዕትነት ለመክፈል ወደኋላ አይሉም፡፡ ይህ መጽሐፍ ወጣቶች በኢስላም ሊኖራቸው ስለሚገባው ኃላፊነት ሐዲስና ቁርኣንን በማጣቀስ ብቻ ሳይሆን የሶሐቦችን፣ የተከታዮችንና የተከታይ ተከታዮችን ተምሳሌትነት ያስነብበናል፡፡ መጅዲ አል ሒላል መጽሐፉን ሲያዘጋጁ የአወሊያ 98 ጀምዐህ ተርጉመውታል፡፡
አዘጋጅ ፡ መጅዲ አልሂላሊ
የገጽ ብዛት ፡ 40
የታተመበት ዓመት ፡ መስከረም 2002
ከመጽሐፉ ፡ በአሁኑ ወቅቱ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ በተለይ ወጣቱ ላይ ያለው ኃላፊነት እጅግ ከባድ ነው፡፡ ይህን ለመገንዘብ ሙስሊሞች ያሉበትን ተጨባጭ ብቻ ማየት በቂ ነው፡፡ ኢስላም በየቦታው ፈተና ዉስጥ ነው፡፡ የኢስላምን ገጽ ለመገንባት የሚለፋው ትንሽ ሲሆን ታዛቢዉና ተመልካቹ ግን ብዙ ነው፡፡  የሥነምግባር ጉድለት በማኅበረሰቡ ዉስጥ ተንሠራፍቷል፡፡ ይህ ሁሉ ዛሬ ላይ ለኢስላም መሥራት በሁላችንም ላይ ግዴታ መሆኑን ያመለክታል፡፡ ለኡማው መውደቅ ሁላችንም ተጠያቂዎች እንደሆንን ልናውቅ ይገባል …
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: