የዕውቀት ኃይል በኢስላም ቁ.1

285.00 Br

አዘጋጅ ፡ ሙሐመድ ዑመር አደም

አሳታሚ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት ኃ/ተ/የግ/ማኅበር

 

ስለመጽሐፉ ይዘት፡

መጽሐፉ በቁጥር አንድ እና ሁለት የተዘጋጀ  ሲሆን በዕውቀት ዙርያ አስፈላጊ የሆኑ ሊታወቁም የሚገቡ በርከት ያሉ በተለያየ ርዕስ ዙርያ የሚያተኩሩ መረጃዎች በተደራጀ መልኩ የታጨቁበት ነው፡፡ ዕውቀት ምን ያህል ኃያል እና አስፈላጊ እንደሆነ ያሳያል፡፡ ሙስሊሙ ለዕውቀት ያለው አመለካከት ከፍ እንዲል ይወተዉታል፡፡

 

ከመጽሐፉ በጥቂቱ

እውቀት:- ጥልቀት የማይርቀው እጅ፤ ርቀት የማያደክመው እግር፤ ድምጽ የማይደብቀው ጆሮ፤ አጣርቶ የሚናገር ምላስ፤ አነፍንፎ የሚደርስ አፍንጫ ነው፡፡ እውቀት:- የሚስጥር ሶላት፤ የነፍስያ ማሰልጠኚያ ጾም፤ ደካሞችን ማስጠለሊያ ዘካ፤ ሰዎችን በእውነት ጥላ ስር የሚያሰባስብ ሃጅ ነው፡፡ እውቀት:- ከቤተሰብ የማይወረስ ሃብት፤ ከገበያ የማይሸመት ንብረት፤ በሽልማት የማይሰጥ ወርቅ፤ በጉልበት የማይነጠቅ ምርኮ፤ በህልም የማይታይ ጸጋ፤ በምኞት የማይገኝ ገንዘብ ነው፡፡ እውቀት:- ስጦታ የማይቀንሰው፤ ቦታ የማይጠበው፤ ሌባ የማይሰርቀው፤ ሸክሙ የማይከብድ፤ እድለኞች የሚያገኙት፤ እድለ ቢሶች የሚያጡት፤ ህልቆ ስፍር የሌለው ሃብት ነው፡፡

በዉስጣችን ያሉ መረጃዎች በየጊዜው ካልተቃኙ ፈጥነው ያፈተልካሉ፤ በቀላሉ ቀለማቸው ይደበዝዛል፤ ከህሊናም ይሰወራሉ፤ የጊዜ መርዘም ተጽዕኖ የማያሳድርበት ነገር የለም፡፡ ቁርኣን ጭምር በየጊዜው ካላዩትና ከተተወ እንደሚጠፋ ነቢዩ ሰ.ዐ.ወ. ተናግረዋል፡፡ …

 

ያንብቡት

ነጃሺ ማተሚያ  ቤት

የእውቀት ማዕድ!!!

************

SKU: M095 Category: