Weight | 148 g |
---|
ወደ አላህ ሽሹ
$5.00
ወደ አላህ ሽሹ/ ፈፍሩ ኢለላህ/ የሰው ልጅ ለሚያጋጥመው ችግር ሁሉ መዳኛው ወደ አላህ መሸሽ ብቻ መሆኑን የምትጠቁም መጽሐፍ ናት፡፡ ሰው ሆኖ የማያጠፋ የለም፡፡ እኛ የሰው ልጆች በኃጢአት እንወድቃለን። ይሁን እንጂ ፈጥነንም እንመለሳለን። ፈጥነን ስንመለስ ተጠቃሚዎች፤ በኃጢኣት ስንዘወትር ተጎጂዎች ነን፡፡ በኃጢአት ላይ የሚዘወትር ሰው ዓይኖቹ ይታወራሉ። ይህ ማለት አካላዊ ዕውርነት ሳይሆን የልቡን ብርሃን የሚያበሩለት ዓይኖቹን ማለት ነው። እንደዚያ በሚሆንበት ጊዜ የፈጣሪውን ብርሃን ማየት አይቻለዉም። ሐቅን መቀበል እስከሚቸገር ድረስም ልቦናው ጽልመት ይለብሳል። መልካምን ነገር ከመጥፎው መለየት ይሳነዋል፡፡
ከኃጢአትም ሆነ ከዚህ ዓለም አደጋዎች ሁሉ መዳን የሚቻለው ወደ አላህ በመሸሽ ብቻ ነው፡፡ መጽሐፉ በተለያዩ የገፆቹ ንዑስ ርዕሦች ሥር ይህን ያስታውሰናል፡፡ ወደ አላህ የምንሸሽባቸዉን መንገዶችና እንዴትነት ይጠቁመናል፡፡
አዘጋጅ ፡ አቡ ዘር አል-ቀለሙኒ
ትርጉም ፡ አሕመድ ሑሴን/አቡ ቢላል
የገጽ ብዛት ፡ 146
የታተመበት ዓመት ፡ 2012
ከመጽሐፉ ፡
አማኞችን ከሚያጠፉ ነገሮች መካከል ትናናሽ ኃጢአቶችን አሳንሶ መመልከት ነው፡፡ ትናንሽ ኃጢአቶች ወደ ታላላቅ የሚያሸጋግሩ ናቸው፡፡ በአንድ የአላህ ባሪያ ዓይን ታላቅ ተደርጎ የሚታይ ኃጢአት በአላህ ዓይን ትንሽ፤ በአገልባጩ ደግሞ በባሪያው ዘንድ ትንሽ ተደርጎ የሚታይ ኃጢአት በአላህ ዓይን ትልቅ ሊሆን ይችላል። የዚህ ዋነኛው ምክኒያት የኃጢአቱ ሁኔታና ባሪያው በልቡ ለኃጢአቱ ያለው የጥላቻ ደረጃ ነው። ኢብን መስዑድ (ረ.ዐ) እንዲህ ብለዋል፡- “አማኝ ሰው ሃጢአቱን ልክ በራሱ ላይ ሊወድቅ እንደሚያንዣብብ ተራራ አድርጎ ይመለከተዋል። ዝንጉ (ሙናፊቅ) ሰው ግን ኃጢአቱን እጁን ቢያወናጭፍ ሊያባርራት እንደሚችል ዝንብ ነው የሚያየው።”(ቡኻሪና ሙስሊም)
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት