ሸይኽ ዐብዱልቃድር ጂላኒ

2.00 $

ሸይኽ ዐብዱልቃድር ጂላኒ ታላቅ የሱፊ ሸይኽና የሸሪዓ ሊቅ ናቸው፡፡ በዘመናዊ ዓለም አስተሳሰብና ምልከታም ያላቸው አሻራ በቀላሉ የሚታለፍ አይደለም፡፡ በመዝሀብ ሐንበሊ ሲሆኑ በመንፈሳዊ ፈለግ የነበራቸው የጠለቀ ስልት ኢትዮጵያን ጨምሮ በበርካታ የዓለማችን ሀገራት ዘወትር እንዲታወሱ አብቅቷቸዋል፡፡
የቁርአን ተፍሲርን ጨምሮ የበረከቱ መንፈሳዊ መዛግብትንም አበርክተዋል፡፡ አንድ የፓኪስታን ታላቅ ተመራማሪ ከሀያ ዓመታት በላይ ረዥም ምርምር ካደረገ በኋላ በአንድነት አዋቅሮ ለህትመት ያበቃልን ተፍሲራቸው በአጭር ጊዜ ከፍተኛ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ ይህ ተፍሲር በ2001 ዓ.ል ለአንባቢያን ደርሷል፡፡
የነበረውን ወርቃማ የኢስላም የጥበብና ስልጣኔ ዘመን ለመመለስ ይቻል ዘንድ የዚያን ዘመን ወርቃማ ሰዎች በመጠኑም ቢሆን በዚህ መጽሐፍ ተዳሷል፡፡
አዘጋጅ ፡ ሙሐመድ ዐሊ
የገጽ ብዛት ፡ 92
የታተመበት ዓመት ፡ 2009
ከመጽሐፉ ፡
መንፈሳዊ ትግል ብዙ ጥረት የሚፈልግ ክዋኔ ሲሆን በኢማን ተራራ ወደ ላይ ከፍ ብሎ ለመገኘትና ድንቅ የተቅዋ አቅም ለመፍጠር የምናደርገው ጥረት ነው፡፡ ሸይኽ ዐብዱልቃድር ጂላኒ በዚህ መስክ ከፍ ያለ ጥናት አድርገዋል፡፡ ጥናታቸውን ለመረዳት ግን ጥቂት ሀሳቦች ስለሱፊዎችና ተሰዉፍ እናያለን፡፡
በዐቂዳ ትምህርት አላህን ብቻ ነጥሎ ማምለክ ግዴታ ነው፡፡ አንድ ሙስሊም ከሺርክ ፍጹም የፀዳ መሰረት እንዲኖረው የሃይማኖቱ ሕግ ነው፡፡ በአላህ መተማመንና ስለሁሉም ነገሮች ምንጭ ፈጣሪው ላይ አቋሙን መያዝ ይኖርበታል፡፡ ይህን ታላቅ የተቅዋ ፀዳል ለመጎናጸፍ ታዲያ ዚክር፣ ዒባዳህ፣ ዙህድ፣ ወዘተ. እያልን በምንጠራቸው መንፈሳዊ ተግባራት ላይ መዘውተር ይኖርብናል፡፡
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: