| Weight | 106 g |
|---|

ሰላማዊ ቤት ምድራዊ ጀነት
180.00 Br
ዝግጅት፡ ዑሥማን ኑሪ ቶፕባሽ
ትርጉም፡ ዐብዱልከሪም ታጁ
አሳታሚ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
ስለመጽሐፉ ይዘትና ማብራሪያ፡
ይህች መጽሐፍ የማህበረሰባችንን ቁስል ለማሻር ጠቃሚ እንደምትሆን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ሰላም የሞላበት ቤት ለመመስረት የሚጠቅሙ መሠረታዊ የኢስላም መርሆዎችንና መረጃዎችን ያገኙባታል፡፡ መጽሐፏ ቤተሠብን በሥርዓት ለመምራት የሚያስችሉ መመሪያዎችንና በየደረጃው መወሰድ ያለባቸውን እርምጃዎች ታብራራለቸ፡፡ ከዕንቁው ዓርአያችን ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እና ከሌሎች ታዋቂ ሙስሊሞች ሕይወት ውስጥ ተያያዥነት ያላቸውን ምሳሌዎች ቀንጭባ ታቀርባለች፡፡ በተቻለ መጠን ግልፅና ቀላል አቀራረብን በመጠቀም የተሻለ ግንዛቤ ለመፍጠር ትሞክራለች፡፡ ስለ ጋብቻና ቤተሰብ ህይወት በኢስላም፣ ለባለትዳሮች የሚያስፈልጉ ጠቃሚ ነጥቦች ከመጽሐፉ በተደራጀ መልኩ ያገኛሉ፡፡
ከመጽሐፉ በጥቂቱ፡
የመጣመርን ባህሪ ይዞ መፈጠር ማለት ወንድና ሴት ሆኖ አንዳችው ሌላኛውን በሚያሟሉበት ሁኔታ መፈጠር ማለት እንጂ በዓይነት ተመሳሳይ ሁኖ በቁጥር ሁለት መሆን አይደለም፡፡ አንድ ዓይነትን ነገር ሁለት ጊዜ መፍጠር ድግግሞሽ ይሆናል፡፡ ድግግሞሽ ደግሞ ለአላህ የሚገባ ባህሪ አይደለም፡፡ ስለዚህ ኃያሉ አላህ ነገሮችን ሁሉ በፆታዊ ጥንድነት ፈጠራቸው ነገር ግን እያንዳንዱ ነጠላ ፍጡር በራሱ ልዩ ነው፡፡ አላህ ፍፁም ተመሳሳይ ነገሮችን ደጋግሞ አልፈጠረም፡፡ ሌላው ቀርቶ በተመሳሳይ መንትዮች መካከል እንኳ በርካታ አካላዊ እና መንፈሳዊ ልዩነቶች ይገኛሉ፡፡
ያንብቡት
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
የእውቀት ማዕድ!!!
************




