| Weight | 168 g |
|---|

ዓፊያ
215.00 Br
አዘጋጅ፡ ጀማል ዐሊ ሙሐመድ
ትርጉም፡ ሙሐመድ ዐብደላ ዐሊ
አሳታሚ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
ስለመጽሐፉ ይዘትና ማብራሪያ፡
ሕይወት እንዳለ ሁሉ ሞትም አለ፤ ጤና እንዳለው ሁሉ በሽታም አለ፡፡ አላህ (ሱ.ወ.) አንድንም በሽታ አልላከም፤ መድኃኒት ያኖረለት ቢሆን እንጂ ፡፡ ሰዎች ግን መድኃኒቱን ሊደርሱበትም ላይደርሱበትም ይችላሉ፡፡ ከበሽታ ለመውጣት ህክምና መሠረት ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ በዓይነቱ የመጀመርያ የሆነ ተፈጥሯዊዉን፣ ነቢያዊዉንና ዘመናዊዉን ሕክምና ባቀናጀ መልኩ ለተለያዩ በሽታዎችና የሰዉነት እክሎቻችን ከሰዉነት ቆዳ ጀምሮ እስከ ዉስጥ ህመም ድረስ መላና መፍትሄ የሚጠቁም በሚገባ ተደራጅቶ የቀረበ አማራጭ ድንቅ መጽሐፍ ነው፡፡
ከመጽሐፉ በጥቂቱ:
ማር በዉስጡ በበቂ ሁኔታ ከአሥራ አምስት በላይ የተለያዩ የስኳር ዓይነቶች፣ ቫይታሚኖች፣ ፕሮቲን፣ የተለያዩ ማዕድናት፣ በርካታ ኢንዛይሞች፣ ፀረ ተህዋሲያን፣ ሆርሞኖች፣ የተለያየ ማዕድናት፣ ፎሊክ አሲድ እና ሌሎችንም.. ያያዘ ነው፡፡
ጥቁር አዝሙድ፣ ነጭ ሽንኩርት፣ እርድ፣ ድኝ፣ ሩማን፣ ለውዝ፣ አብሽ፣ ፖም፣ የወይራ ዘይት፣ ሙዝ፣ እንቁላል፣ ዝንጅብል፣ … እና ሌሎችም በርካታ አትክልት፣ ፍራፍሬዎች፣ ጥራጥሬዎችና ቅጠላ ቅጠሎች በሕክምናው ዓለም ዉስጥ ያላቸዉን ሚና በዚህ መጽሐፍ ዉስጥ እንቃኛለን፡፡ …
ያንብቡት
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
የእውቀት ማዕድ!!!
************




