የኢስላም ሁለንተናዊነት ክፍል ሁለት

180.00 Br

አዘጋጅ ፡ ዶ/ር ዐብደላህ አልቀሕጣኒ

ትርጉምና ዝግጅት ፡ አሕመድ ሑሴን (አቡ ቢላል)

አሳታሚ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር

 

ስለመጽሐፉ ይዘትና ማብራሪያ፡

ኢስላም ሰማያዊዉን ዓለም ለመውረስ ብቻ የሚከተሉት ሃይማኖት  አይደለም፡፡ ኢስላም የዚህንም ሆነ የመጨረሻዉን ዓለም ስኬት የሚጠቁም ሁለገብ መመሪያ ነው፡፡ ኢስላም ሁሉን አቀፍና ሁለንተናዊ ነው፡፡ የሰዉን ልጅ የሕይወት ጎኖች ሁሉ ይዳስሳል፡፡ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ሥነልቦናዊ፣ ፖለቲካዊ .. ሁሉንም ይነካካል፡፡ ይህ መጽሐፍ የተለያዩ ጉዳዮችን በማንሳት የኢስላምን ሁለንተናዊነት ጠለቅ ባለ ሁኔታ ይዳስሳል፡፡ ኢስላም ከሳይንስና ከፖለቲካ አንፃር ያለው እይታ በስፋት የቀረበበት በሁለት ክፍሎች የቀረበ መጽሐፍ ነው፡፡

 

ከመጽሐፉ ፡

ሙስሊሞች ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ እግዚአብሔር ልጅ ሳይሆን እንደ ነቢይ ይቀበሉታል። የማርያምን የኢየሱስ እናትነት ይቀበላሉ። አዳምን፣ ኖህን፣ አብረሃምን፣ ሙሴን፣ ያዕቆብን ያውቃሉ። የመንግስተ ሰማያትንና የገሃነምን ጽንሰ ሐሳብ ያምናሉ። መንግስተ ሰማያት በረሃ ያልሆነ አትክልትና ወንዞች የሚፈስሱበት እንደሆነ፣ ገሃነም ደግሞ ኃጢያተኞች ቆዳቸው እስኪላጥ ድረስ የቀለጠ ብረት የሚጠጡበትና የዘላለም አካላዊና አእምሮአዊ ስቃይ የሚከፍሉበት እንደሆነ ይቀበላሉ።

 

ያንብቡት

ነጃሺ ማተሚያ  ቤት

የእውቀት ማዕድ!!!

************

 

 

SKU: M034 Category: