| Weight | 85 g |
|---|

የወላጅ ሐቅ
184.00 Br
ዝግጅት፡ ዐብዱልመሊክ ቃሲም
ትርጉም፡ ሑሴን ኸድር
ስለመጽሐፉ ይዘትና ማብራሪያ፡
ኢስላም ለወላጆች ትልቁን ቦታ አጐናጽፏቸዋል፡፡ አላህ ከራሱ አምልኮ ቀጥሎ የወላጆችን ጉዳይ አደራ ብሏል፡፡ ወላጆችን አስመልክቶ በርካታ የቁርኣን አንቀጾች ቁርኣን ውስጥ እናገኛለን፡፡ ይህም ሆኖ በአሁኑ ዘመን የወላጆች ደረጃ እየተዘነጋ የመጣ ይመስላል፡፡ አንዳንድ ልጆች በወላጆቻቸውና በነሱ መካከል ያለውን ርቀት ከመዘንጋት አልፈው ወላጆቻቸውን የመናቅ የማንኳሰስ ስሜትን እያሳዩ ነው፡፡ በሥነ-ምግባር የተበላሹ ልጆች የመኖራቸውን ያህል ለወላጆቻቸው ቅንና ታዛዥ የሆኑ ልጆችም አሉ፡፡ የመጽሐፉ አዘጋጅ ለወላጆች ቅን ስለመሆን፣ በወላጆች ላይ የማመጽ አደገኛነትና ስለ ሌሎችም ተያያዥ ጉዳዮች አውስቷል፡፡
ከመጽሐፉ በጥቂቱ:
“አቡበክር” የተባሉት ታላቅ ዓሊም ‘ዛዱል ሙሳፊር’ በተሰኘው መጽሐፋቸው ‘አንዳች ነገር በመሥራቱ ወላጆቹ የተቆጡት ወይም ያለቀሱበት (ሰው) በፍጥነት አንዳች የሚያስደስታቸውን ወይም የሚያስቃቸውን ነገር ማድረግ አለበት።’ ይህ ማለት ወላጆች አንዳች የሚያስፈልጋቸው ነገር ሲያዙ ፈጥኖ በመታዘዝ አክብሮትን ማሳየት ነው። ማንኛውንም ትዕዛዛቸውን በፍጥነት መፈጸም ማንኛውንም የማይፈልጉትን ነገር መተው ተገቢ ነው። …
ያንብቡት
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
የእውቀት ማዕድ!!!
************




