ኢስላም የማህበራዊ ችግሮች መፍትሄ

280.00 Br

አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር

 

ይዘት፡

ይህ ዘመን በሰው ዘር ታሪክ ውስጥ ተወዳዳሪ የማይገኝለት የጽልመት ዘመንን እንደሚወክል ይታመናል፡፡ ይህ መጽሐፍ ደግሞ አጠቃላይ የማኅበራዊ ችግሮች መፍትሔ ምን እንደሆነ ጠቁሞ መፍትሔውም ኢስላም መሆኑን ይነግረናል፡፡ ኢስላም ማኅበራዊ ሥርዓትን በምን መልኩ እንደሚያስተናግድ የሚገልጽ፤ የምዕራቡ ዓለም ማኅበራዊ ቀውስን እና ሌሎችንም ጉዳዮች በሰባት ምዕራፍ የሚያሳይ መጽሐፍ ነው፡፡ በኢስላም ላይ የሚነሱ አንዳንድ ጥያቄዎችን በማንሳትም ያብራራል፡፡ ለዓለማችን ችግሮች ከኢስላም በላይ መፍትሄ አለመኖሩን በማስረጃ አስደግፎ ያስቀምጥልናል፡፡

 

ከመጽሐፉ በጥቂቱ፡

ወሲባዊ ጥምረት ለቤተሰብ ምስረታና መረጋጋት ዓይነተኛ መንገድ መሆኑን የሚያስተምረው የኢስላም ሃይማኖት ቤተሰብን ሊያጠናክሩና ዘላቂ ማድረግ የሚያስችል ስልቶችንም ነድፏል። በዚህ ረገድ ይህ ሃይማኖት የተፈጥሮ ሕግን የተለያዩ ገጽታዎችና ፈርጆች ከግንዛቤ አካቷል። የባልና የሚስት መብትና ግዴታን (ሐቅ) በተመለከተ ፍትሀዊ  የሆኑ መርሆችን ደንግጓል። እነኚህን ድንጋጌዎች በቅጡ ስንገመግም የምናገኘው ቁም ነገር ኢስላም በሁለቱ ጾታዎች መካከል መኖር የሚገባውን እኩልነት ያሰፈነ መሆኑን ነው።

 

ያንብቡት

ነጃሺ ማተሚያ  ቤት

የእውቀት ማዕድ!!!

************

 

 

 

SKU: M004 Category: