| Weight | 67 g |
|---|

ለምን ተፈጠርን?
90.00 Br
ዝግጅት፡ አቡ አሚና ቢላል ፊሊፕስ
ትርጉም፡ አብይ ጣሰው
አሳታሚ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
ስለመጽሐፉ ይዘትና ማብራሪያ፡
ይህ መጽሐፍ ስለ ፍጥረተ ዓለሙ ፈጣሪ ህያውነት አመላካች የሆኑ ነገሮችን በመዘርዘር ለኢ-አማንያን ምላሽ የሚሆኑ ማስረጃዎችን ከቁርኣን እያጣቀሰ ይተነትናል፡፡ በዚህ ብቻ ሳይወሰን የሰውን ልጅ የመፈጠሩ ዓላማ ለምንታን (ለምን-ተፈጠረ) ለማስረዳት በርካታ ማሳያዎችን ያስቀምጣል፡፡ በርግጥም የሰው ልጅ ማን እንደፈጠረውና ለምን ዓላማ እንደተፈጠረ ሊያውቅ ይገባል፡፡ ፈላስፎች በየጊዜው ከየራሳቸው ግምት ተነስተው ሰውን ወደ ተቀበዣዠረ አመለካከት ሲከቱት ቆይተዋል ቁስ አካላውያን “የሰው ልጅ እዚህ ምድር ላይ ለመገኘቱ ዓላማ የለውም” የሚል አቋም ይዘዋል፡፡ አዘጋጁና ዕውቁ ዳዒ በዚህ መጽሐፉ ከዚህና ከሌሎችም የዓለማውያን ቅብጥርጥር ተነስቶ አላህ የሰውን ልጅ ለምን እንደፈጠረ ግልጽ አድርገው ያሳዩበት መጽሐፍ ነው፡፡
ከመፅሐፉ በጥቂቱ፡
እያንዳንዱ ሰው ቢያንስ በሕይወቱ አንድ ጊዜ “ለምን ተፈጠርኩ ?” ወይም “ለምን ጉዳይ በዚህ ምድር ላይ ተገኘሁ ?” ብሎ መጠየቁ አይቀርም፡፡ የመፈጠር ዓላም የሰው ልጅ በሕይወቱ እስካለ ድረስ የሚጠይቀው ጥያቄ ነው፡፡ የሥራ መኖር ሠሪ እንዳለ እንደሚያመለክተው ሁሉ የዚህ ፍጥረተ ዓለምና የሰው ልጅ ዉስብስብ አወቃቀር አንድ ኃያል ፈጣሪ እንዳለ ያመለክታሉ፡፡ …
ያንብቡት
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
የእውቀት ማዕድ!!!
************




