
ሐጅ እና ዑምራ
150.00 Br
አሳታሚ ነጃሺ ማተሚያ ቤት
አዘጋጅ ፡ ሙሐመድ ሰዒድ
ስለመፅሃፉ ጥቂት ማብራሪያ
መጽሐፉ በሐጅ እና ዑምራ ዙርያ መሠረታዊ ትምህርቶች እና መመርያዎችየተካተቱበት ነው፡፡ ለመጀመርያ ጊዜ ሐጅ ወይም ዑምራ የሚሄዱ ሰዎች እንደ ማመላከቻና ማጣቀሻ ሊጠቀሙበት የሚገባ ነው፡፡
ከመጽሐፉ በጥቂቱ፡
አባትና ልጅ ነቢዩ ኢብራሂም እና ነቢዩ ኢስማዒል ግንባታውን ካጠናቀቁ በኋላ ሰዎች ይጎበኙት ዘንድ ጥሪ እንዲያደርጉ አላህ (ሱ.ወ.) ነቢዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ.) አዘዛቸው። እርሳቸውም ለሐጅ ጥሪ አደረጉ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የያኔ ጥሪ ደርሷቸው አቤት ያሉ ነፍሶች ሁሉ አላህ አድሏቸው የአላህን ቤት ለመጎብኘት ወደ መካ ያቀናሉ። ለጥሪው ምላሽ የመስጠቱ ሒደት እስከ ዕለተ ትንሳኤ ድረስ የሚቋረጥ አይደለም። የአላህ ቤት ቀንና ሌሊቱን 24 ሰዓታትና ዓመቱን ሙሉ ያለማቋረጥ ከተለያዩ የዓለም ሁሉም ማዕዘናት ወደዚያ በሚጎርፉ ምእመናን ይጎበኛል።
ያንብቡት
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
የእውቀት ማዕድ!!!
************




