በዓለም ላይ እጅግ ደስተኛዋ ሴት መሆን ትቺያለሽ

240.00 Br

ዝግጅት፡ ዶክተር ዓኢድ  አልቀርኒ

ትርጉም፡ ሱለይማን ጠይብ

“በዓለም ላይ እጅግ ደስተኛዋ ሴት መሆን ትቺያለሽ” በሚል ርዕስ ወደ አማርኛ የተመለሰው ይህ የዶክተር ዓኢድ አልቀርኒ መፅሐፍ በተለይ ለሴቶች የታለመ ሆኖ ዘመናዊው ሰው ያጣው ምርጥ የሕይወት ቅመም -ደስታ-የሚገኝባቸውን መንገዶች ያመላክታል፡፡ከቁርኣን ፣ከሐዲስ ፣ከሲራና ከታሪክ ገጠመኞች እና ትረካዎችንም በአስተማሪነት ተጠቅሟል፡፡የመፅሐፉ ዓላማ ሴቶች ደስታን የሚያገኙባቸውን መንገዶች ማመላከት ሲሆን ጭንቀት ፣ ትካዜና ሐዘን ከመከሰታቸው በፊት መከላከል የሚቻልባቸውን መንገዶችም ይጠቁማል፡፡ከዚህ ባለፈም ችግርና መከራ በሚያጋጥም ጊዜ የሥነ ልቦና መሠባበርና ቀቢጸ ተስፋ እንዳይከተሉ መወሰድ ባለባቸው እርምጃዎች ላይም ሃሳብ ያነሳል፡፡ባጠቃላይ የዘመናዊው ሰው መገለጫ የሆነውን ደስታ የማጣት ችግር ለማስወገድና የተድላ ሕይወት ለመግፋት የሚያስችል መመሪያ ነው ማለት ይቻላል፡፡

መጽሐፉ ዶክተር ዓኢድ አልቀርኒ “አስዐድ ኢምረኣ ፊልዓለም” በሚል ርዕስ ያዘጋጁት መፅሐፍ ትርጉም ቢሆንም ዶክተሩ በዐረቢኛ ቋንቋ ካዘጋጁት መፅሐፍ በቀጥታ ወደ አማረኛ የተመለሰ አይደለም፡፡ይህ ትርጉም ሁዳ ኸጧብ “You can be the Happiest Woman in the World-a Treasure Chest of Reminders” በሚል ርዕስ በእንግሊዝኛ ካዘጋጁት የትርጉም ሥራ ለአገራችን ታዳሚዎች በአማረኛ ቋንቋ የተሰናዳ የትርጉም ትርጉም ነው፡፡

SKU: S012 Category: