
ሴትነት በኢስላም
275.00 Br
ሴትነት በኢስላም
አዘጋጅ:- ኡስታዝ ሙሐመድ ዑመር አደም
የገጽ ብዛት ፡ 272
የታተመበት ዓመት ፡ ሐምሌ 2017
ይዘት ፡
መጽሐፉ በሦስት ምዕራፎች የተከፈለ ሲሆን በቀዳሚው ምዕራፍ ስለ ሴትነት፣ የሴት ልጅ መለያ፣ ስለ አልባሳቷ፣ ስለ ውበት፣ ስለ ፍቅር፣ ስለ መጣመር፣ ስለ ፆታዊ ግንኙነት፣ ስለ እናትነት፣ ስለ የሥራ አስፈላጊነትና ስለ ፍች ይዳስሳል፡፡ በሁለተኛው ምዕራፍ ሥር ሴት ልጅ በሰውነቷ፣ ሚስት ሆና፣ እናት ሆና፣ እህት ሆና ስላላት መብትና ክብር ተዳሶበታል፡፡ እንዲሁም ስለ ማኅበራዊ፣ ዕውቀታዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና መንፈሳዊ መብቷ በዝርዝር ተዳሶባትል፡፡ በሦስተኛ ምዕራፍ መንታ መንገድ በሚል ርዕስ ሥር ልዩነት ወይስ ወጥነት?፣ ፍትሕ ወይስ እኩልነት፣ ልቅነት ወይስ ነጻነት፣ አካላዊ ወይስ አእምሯዊ ሥልጣኔ፣ ባህል ወይስ ኢስላም፣ ሰውኛ ወይስ የፈጣሪ ሕግ፣ ለዓለማዊ መሻት ወይስ ለዓላማ መኖር?! … የሚሉ ንዑስ ርዕሶችን ይዳስሳል፡፡
ከመጽሐፉ ፡
አላህ አደምን ከፈጠረ በኋላ፣ ባለቤቱን ከገዛ አካሉ (ከአደም) አስገኛት። አደምም ሕያው ከሆነ አካሉ ላይ የተፈጠረች በመሆኗ ስሟን ሐዋ ብሎ ሰይማት። ከርሷ በኋላ ከብቸኝነት አርነት ወጣ። የሚሹትን እየበሉና እየጠጡም በተድላ መኖር ጀመሩ። ከአንድ ዛፍ በቀር ሁሉም ነገር ለነርሱ ተፈቀደ። አንድ ዕለት፣ ሰይጣን ብቅ ብሎ፣ “ይህችን ዛፍ የተከለከላችሁት ዘላለማዊ ክብርና ንግሥናን እንዳታገኙ ነው” በማለት ወተወታቸው። በውትወታውና በመሐላው ተሽንግለውም ስህተት ላይ ወደቁ። ዛፏን ከነኩ በኋላ የተሰተሩባቸው አልባሳት ከላያቸው ላይ በረሩ። እርቃናቸውን ሲቀሩ በሥፍራው በሚገኙ ቅጠሎች ሰውነታቸውን መሸፈን ጀመሩ። ትዕዛዙን በመጣሳቸውም ተወቀሱ። ከተደላደሉበት የክብር ቦታም እንዲወገዱ ተደረጉ። ከዚህ በኋላ በምድር ላይ ኑሯቸውን ለመምራት መኳተን ጀመሩ። ‹ይህ የሁላችንም እናት የሆነችው የመጀመሪያዋ እንስት አጭር ታሪክ ነው።›




