አርዓያ (ክፍል አንድ)

335.00 Br

አዘጋጅ ፡ ኡስታዝ ሙሐመድ ዑመር አደም

አሳታሚ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር

 

ይዘት:

መጽሐፉ በነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) የተግባባቶች መንገዶች ዙርያ የተፃፈ ነው፡፡ በዘጠኝ ክፍሎች ተከፍሎ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ሰዎችን ስለሚያውቁበት መንገድ፤ ስሜታቸውን እንዴት እንደሚቆጣጠሩ፤መልዕክታቸውን በምን መልኩ እንደሚያስተላልፉ፤እንዴት ሰዎችን ለማሳመን እንደሚጥሩ፤ስልታዊ አቀራረባቸው እንዴት እንደሆነ፤ትኩረታቸውን እንዴት እንደሚስቡ፤መርሳት እንዳይችሉ አድርገው እንዴት እንደሚያስረዱ፤ለተግባርም እንዴት እንደሚያነሳሱና ሚዛናዊውን መንገድ እንዴት እንደሚከተሉ ይዳስሳል፡፡

 

ከመጽሐፉ፡

ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ከፍተኛ በሆነ የንግግር ጥበብ የተካኑ ከመሆናቸው ጋር ለተግባቦት ትኩረት ይሰጡ ነበር። ቁርኣንም፣ ‹‹ውስጣቸውን ዘልቆ የሚገባ ትምህርት ስጣቸው።›› (አን-ኒሳእ፡63) በማለት ያዛቸዋል። ከዚህም የተነሳ የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ንግግሮች በአንድ ጊዜ አእምሮንም ስሜትንም መንካትና ማናገር የሚችሉ ናቸው። ባልደረቦቻቸው፡- ‹‹የአላህ መልዕክተኛ ቀልቦችን በፍርሃት የሞላ፣ ዓይኖችን በእንባ ያራጨ ምክርና ተግሳጽ ለገሱን።›› (ሙስሊም) በማለት ምስክርነታቸውን ይሰጡ ነበር።

 

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) በወጉ ያልተደራጀና አሰልቺ ንግግር ማድረግ የብስለት ማነስ መሆኑን ሲገልጹ፡- ‹‹የአንድ ሰው ንግግሩ ማጠሩ፣ ዕውቀቱን አመልካች ነው።›› በማለት ተናግረዋል። (ሙስሊም)።

 

ሐሳቡን አደራጅቶ በትክክል እውነትን የሚገልጽ ሰው አላህ ዘንድ የላቀ ክፍያ አለው። ይህን አስመልክተውም፣ ‹‹መልካም ንግግር ምጽዋት ነው።›› በማለት ተናግረዋል። (ቡኻሪ)

 

 

ያንብቡት

ነጃሺ ማተሚያ  ቤት

የእውቀት ማዕድ!!!

************

 

SKU: T058 Category: