ዝግጅት ፡ ዶ/ር መጅዲ አል-ሂላሊ
ትርጉም ፡ ሙሐመድ ሰዒድ (ABX)
ይዘት፡
ይህ መጽሐፍ በሕይወታችን ዉስጥ ቅድሚያ ሊሠጠው ስለሚገባ ነገር በዝርዝር ይዳስሳል፡፡ ስለ ኢማን፤ኢማን ላይ ትኩረት እንድናደርግ፣ ለኢማን እንድንለፋ፣ ለኢማን እንድንሠራ፣ በኢማን እንድንበረታ ያነሳሳል፡፡ ከሁሉ ነገር ኢማን/እምነት ይቀድማል፤ ሰው ካላመነ አይነሳሳም፣ አይበረታታም፣ አይሠራም፣ አይለፋም፡፡
ከመጽሐፉ፡ አንድ ሰው አላህን የአላህ ባርያ መሆኑ ሙሉ ማንነቱን እና ስሜቱን ለሱ በማስገዛት ዉስጥ ይገለፃል። ለሱ ብሎ መውደድ፣ ለሱ ብሎ መጥላት፣ እሱን መታዘዝ፣ ቢከለክለው መከልከል፣ በችሮታው መደሰት ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም ከአላህ አንፃር ካሳየው ጉድለቶች አንፃር ማዘን፣ በመመሪያው መዳኘት፣ ለሱ ብሎ ሙግት መግጠምም እሱን የማምለክ መገለጫ ነው። ሙሉ በሙሉ ለአላህ እጅ መስጠት መነሻው፡፡ አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ይላል፡- “ስግደቴ፣ መገዛቴም፣ ሕይወቴም፣ ሞቴም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ነው” በል፡፡ ለእርሱ ተጋሪ የለውም፡፡ በዚህም (በማጥራት) ታዘዝኩ፡፡ እኔም የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ፡፡(በል)፡፡” የሚለዉን የአላህን (ሱ.ወ) ቃል እውነትን ለማረጋገጥ ነው፡፡
ያንብቡት
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
የእውቀት ማዕድ!!!
************





