የህሊና ዕረፍት ቁጥር ሦስት

105.00 Br

ዝግጅት፡ ዶ/ር  ሙሐመድ  ሰዒድ(ABX)

አሳታሚ፡ ነጃሺ ማተሚያ  ቤት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር

 

ስለመጽሐፉ ይዘትና ማብራሪያ፡

በአጫጭር ዐረፍተነገር ከጠቢባን፣ ከቀደምት ደጋግ የአላህ ባሮች እና የኢማን ሰዎች አንደበት የሚፈልቁ ቁምነገሮች እምቅ ትርጉምና ምትሃታዊ መልዕክት አላቸው፡፡ ሳይታሰብም ለብዙዎቻችን ትልቅ ትምህርትን ሠጥተው ያልፋሉ፡፡ ኢማናችንንም ያድሳሉ፡፡ ይህ መጽሐፍ በአጫጭር መልዕክቶችና አባባሎች ትላልቅ ቁምነገሮችን የሚያስታውስና የሚያስተምር ነው፡፡

 

ከመጽሐፉ በጥቂቱ፡

  • ሣንለምንህ ሁሉን ነገር የሰጠኸን ጌታችን ሆይ! በለመንህ ጊዜ ከችሮታህ አትከልክለን ። ፀጋህን አትያዝብን ።
  • እየሸሸንህ የጠራኸን አምላካችን ሆይ ! በመጣንና ፊታችን ወዳንተ በዞርን ጊዜ ተቀበለን አትመልሠን ።
  • በዚህች ዓለም ላይ ሣለን መጥፎ ወንጀሎቻችንን ሁሉ እያየህ የሠተርከንና ያለፍከን ፈጣሪያችን ሆይ ! ነገም በአኺራ በጭንቁ ቀን አታጋልጠን ።
  • እያጠፋን የታገስከን አምላካችን ሆይ! በታዘዝንህ ጊዜ ጥረታችንን መዝግብልን ሩጫችንን ፃፍልን ።

 

ያንብቡት

ነጃሺ ማተሚያ  ቤት

የእውቀት ማዕድ!!!

************

 

 

 

 

SKU: M019 Category: