| Weight | 110 g |
|---|

ሰው እና ሰይጣን
180.00 Br
አዘጋጅ፡ ሙሐመድ ሙተወሊትዋሊ አሽ-ሸዕራዊይ
ትርጉም፡ ዒማዱዲን ዙልፊቃር
አሳታሚ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
ስለመጽሐፉ ይዘትና ማብራሪያ፡
ለመኾኑ ሰይጣን ማን ነው! ከአእምሮአችን ውል የሚልና መልስ የማይገኝለት የዘወትር ጥያቄ፡፡ ሰይጣን ረቂቅ ፍጡር ነው፡፡ ስለዚህም እርሱ እንደሚያየን ሁሉ በዐይናችን በብረቱ እንመለከተው ዘንድ አይቻለንም፡፡ ሲሻው በውል ከማንለየው አድራሻ(ሥፍራ) ኾኖ ሥርአተ ሃሳባችንን እንዳሻው ይዘውረዋል፡፡ በል ሲለው ከየ እዝነልቦናችን በመጠጋት በረቂቅ ቃላቱ ክፋቱን ያንሾካሹካል፡፡ ይህንና ተያያዥ ጥያቄዎችን መጽሐፉ ይመልስልናል፡፡
ከመጽሐፉ በጥቂቱ :
የተረገመው ሰይጣን ለአደም እና ዘርማንዘሩ ጠላትነትን ያወጀ እኩይ ጠላት ነው፡፡ አጅሬው ሰይጣን ‘ለአደም (ዐ.ሰ) መስገድ አሻፈረኝ’ ብሎ ካመፀባት ቅፅበት ጀምሮ በአድራጎቱ የመፀፀትም ኾነ እውነታውን የመቀበል ፍላጎት አላሳየም፡፡ ‘ጌታዬ ሆይ! ቃልህ እውነት ናት፡፡ ትዕዛዝህም እንዲሁ፡፡ ማረኝ;’ አላለም፡፡ በትምክህቱ በመቆጨት ተነስቶ አልሰገደም፡፡ እንዲያውም በትዕቢት አበጠ፡፡ በግትር ኩነኔውም ፀና፡፡ …
ያንብቡት
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
የእውቀት ማዕድ!!!
************




