Weight | 69 g |
---|
500 የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ባህሪያት
1.00 $
ያለንበት ዓለማቀፍ ሁኔታዎች የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ.) መንገድ አጥብቀን እንድንከተል የሚያደርጉን ናቸው፡፡ ለርሣቸው ፍቅራችንን መግለጽ የምንችለው መንገዳቸዉን በመከተል፣ ባህሪያቸውን በመላበስ፣ አስተምህሮታቸውን በማሠራጨት፣ ፈለጋቸውን በመውረስና በሌላም መልኩ ነውል፡፡ ይህች አነስተኛ መጽፍም ስለ አላህ መልዕክተኛ አካላዊም ሌሎች ባህሪዎችና መገለጫዎች የተዳሰሱባት ናት፡፡
ትርጉም ፡ ሙሐመድ ሰዒድ
የገጽ ብዛት ፡ 60
የታተመበት ዓመት ፡ግንቦት 2007
ከመጽሐፉ ፡
የምእመናን እናት እናታችን ዓኢሻ (ረ.ዐ.) ስለ አላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) ባህሪ በተጠየቁ ጊዜ ‹ ባህሪያቸው ቁርኣን ነበር፡፡ እሱ ለተቆጣበት ነገር ይቆጣሉ፡፡ ቁርኣን የወደደውን ነገር ይወዳሉ፡፡ ለራሳቸው ብለው አይበቀሉም፡፡ ለራሳቸው ጉዳይ አይቆጡም፡፡ የአላህ ህግጋት የተጣሰ እንደሆነ ግን ለአላህ (ሱ.ወ.) ብለው ይቆጣሉ፡፡ የተቆጡ እንደሆነ ደግሞ ቁጣቸው ፊት ማንም አይቆምም፡፡› ብለዋል፡፡
ከነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ባህሪያት
1. ያገኙትን ሰው በሰላምታ ይቀድማሉ፡፡
2. ያለ ጉዳይ ወይም ያለምክንያት አይናገሩም፡፡
3. እጅግ ቸርና እጅግ ለጋስ ናቸው፡፡
4. ወደኋላ ዞረው ሲመለከቱ ሙሉ በሙሉ ነው የሚዞሩት፡፡
5. ዝምታ ያበዛሉ፡፡ ትካዜያቸው ተከታታይ ነው፡፡
6. በክብር የተሸለመ ግርማ ሞገስ አላቸው፡፡
7. ለዓለማት ህዝብ ሁሉ መስተካከል ያስባሉ፣ ይጨነቃሉ፡፡
8. ከኩራት፣ ከመመፃደቅና ከጉራ የራቁ ናቸው፡፡
9. ለተመለከታቸው ሁሉ የሚስብ ነገር አላቸው፡፡
10. ትንሿን የአላህ (ሱ.ወ.) ፀጋ እንደ ትልቅ ያያሉ፡፡
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት