450 ሶሒህ ሐዲሦች

3.00 $

ኢማም ቡኻሪ ያሰናዱት “ሶሒሕ አል-ቡኻሪ” መጽሐፍ እጅግ ተኣማኒነት ካላቸው የሐዲሥ መጽሐፎች መካከል በመጀመርያ ደረጃ የሚጠቀስ መጽሐፍ ነው፡፡ መጽሐፉ በከፍተኛ ድካምና ልፋት ተስብስበው የተጠናቀሩ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ነብያዊ ሐዲሦችን ይዟል፡፡ ይህ መጽሐፍ በተለያየ ጉዳይ ላይ ያተኮሩ፤ ከሶሒሕ አል-ቡኻሪ የተውጣጡ 450 ምርጥ ነቢያዊ ሐዲሦች የተካተቱበት ነው፡፡
አዘጋጅ ፡ ኢማም ዘይነዲን አሕመድ ኢብን ዐብዱለጢፍ
ትርጉም ፡- ዶ/ር ኢድሪስ ሙሐመድ
የገጽ ብዛት ፡ 135
የታተመበት ዓመት ፡ 1993
ከመጽሐፉ ፡ ከአቢ ሙሳ (ረ.ዐ.) እንደተላለፈው ሰዎች የአላህ መልዕክተኛ ሆይ የማን ኢስላም በላጭነት አለው በማለት ጠየቋቸው፡፡ እርሣቸዉም “ሙስሊሞችን በምላሱ እና በእጁ የማይጎዳ፡፡” በማለት መለሱ፡፡
አነስ (ረ.ዐ.) እንዳስተላለፉት ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) “አንዳችሁም እምነት ሊኖረው አይችልም ለራሱ የሚወደዉን ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ፡፡”

አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: