400 ኢስላማዊ አባባሎችና ጥበባዊ ንግግሮች

3.00 $

ይህ መጽሐፍ ውድ የሆኑ የሰሐባ፣ የታቢዒና አዋቂ ጥበበኞች ሰዎች አባባሎችን ያሰባሰብኩበት ነው፡፡ የነዚያ ሥራቸውን ለአላህ ብቻ አጥርተው የሰሩ ስብእናዎች፡፡ ለአላህ ብቻ ስለሰሩም ነው ቀልባቸው የጥበባዊ ንግግሮች መፍለቂያ ልትሆን የቻለችው፡፡ ከአንደበታቸው የምትወጣው እያንዳንዷ ቃል ለሁሉም ጥበብ ፈላጊ የቅናቻ ብርሃን ናት፡፡ እስልምናና ለዕውቀት ስላበረከቱት አስተዋጽኦ ሁሉ አላህ በመልካም ይመንዳቸው፡፡ እኛንም መልዕክቶቻቸውን ለመተግበር ከሚታደሉት ያድርገን፡፡ በድርጊቶቻቸው የምንመራም ያድርገን፡፡
አዘጋጅ ፡ ሸይኽ ኡሳማ ነዒም ሙስጠፋ
ትርጉም ፡ ሙሐመድ ሰዒድ
የገጽ ብዛት ፡ 96
የታተመበት ዓመት ፡ 2008
ከመጽሐፉ፡
‹የአላህ ፍራቻ ትልቅ ሀብት ነው፡፡ ብልህ ሰው ነፍሱን የመረመረና ከሞት በኋላ ላለው ሕይወቱ የሠራ ነው፡፡ ከአላህ ብርሃንም በመቃብር ውስጥ ብርሃን ሊሆነው የሚችልን ነገር የወሰደ ነው፡፡ አንድ ባሪያ ዐይናማ የነበረ ሲሆን አላህ እውር አድርጎ እንዳይቀሰቅሰው ይፍራ፡፡ ጥበበኛ ሰው አጠቃላይ የሆኑ ንግግሮችን ይናገራል፡፡ ደንቆሮ ከሩቅ ይጣራል፡፡ ልብ በሉ! ለአላህ የሆነ ሰው ምንም የሚፈራው ነገር አይኖርም፡፡ አላህ በሱ ከሱ አንጻር የሆነ ሰው ደግሞ መጠጊያም ሆነ ከለላ አይኖረውም፡፡” ዑሥማን ኢብኑ ዐፋን
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: