24 ሰዓት በሙስሊም ህይወት

3.00 $

መጽሐፉ ሙእሚን በ24 ሰዓት ውስጥ ሊኖረው የሚገባውን ሕይወት የሚያመለክት ነው፡፡ ቁርኣንን መሠረት ያደረገ የአንድ ሙስሊም ሕይወት ምን ይመስላል? ሙስሊም ከእንቅልፉ ከነቃበት ጊዜ አንስቶ ለመኝታ ጎኑን እስከሚያሳርፍ ድረስ እንዲሁም ሌሊቱን በምን መለኩ ማሳለፍ አለበት? የሚለውን መጽሐፉ ቁርኣንና ሐዲስን መሠረት አድርጐ ማብራሪያ ይሰጣል፡፡ የኢስላምን ሁለንተናዊነት በተፈኩር የተሞላ ጽሐፍ ነው፡፡
አዘጋጅ ፡ ሃሩን የሕያ
ትርጉም ፡ ኢዘዲን አባፊጣ
የገጽ ብዛት ፡ 112

ከመጽሐፉ ፡ አንዳንድ ሰዎች ሃይማኖትን የሚረዱት በተወሰነ ጊዜ ውስጥ የሚከናወን ጸሎት አድርገው ነው። በሌላ አነጋገር ሰዓታትን ከፋፍለው ጥቂቱን ለአምልኮ ቀሪውን ደግሞ ለሌሎች ጉዳዮቻቸው ማዋል እንዳለባቸው ያስባሉ። አላህ (ሱ.ወ)ወይም የትንሳኤ ቀንን የሚያስታውሱት ሲሰግዱ፣ ሲጾሙ፣ ሰደቃ (ምጽዋት) ሲሰጡ ወይም ሐጅ ለማድረግ ወደ መካ ሲጓዙ ብቻ ነው። ለነዚህ ተግባራት ከሚያውሉት አጭር ጊዜ ውጭ ያለውን አብዛኛውን ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት ዘውታሪ ላልሆኑ ምድራዊ ፍላጎቶቻቸው ሲጨነቁና ሲጠበቡ ነው። በመሆኑም ሕይወት ማለት ለነርሱ ሌላውን በልጠው ለመገኘት የሚፍጨረጨሩበትና የማይቋጭ የሆነ ስኬት አልባ ትግል ነው። እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች ከሞላ ጎደል ከቁርኣናዊው የሕይወት መርህ ያፈነገጡ መሆናቸው ለዚህች ዓለም የራሳቸው የሆነ ዕይታና ትርጉም እንዲኖራቸው አድርጓቸዋል።
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category:

Additional information

Weight 112 g