የባዶነት ስሜት እና መንስኤው

420.00 Br

አዘጋጅ፡ ያስሚን ሙጃሂድ

ትርጉም፡ በሱለይማን ጦይብ

ነጃሺ ማተሚያ  ቤት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር

 

ስለመጽሐፉ ይዘትና ማብራሪያ፡

መጽሐፉ በዋናነት ሥነልቦናዊ  ሲሆን የሰው ልጅን  የሚያጋጥሙት ችግሮች፣ተግዳሮቶች እና ቁስሎች በምን መልኩ መያዝና መታከም እንዳለባቸው መንገድ ያመላክታል፤ መፍትሄ ይጠቁማል፡፡ ከቁስሎች ማገገም እንዴት እንደሚቻል ኋላም በምን መልኩ ወደ አዲስ ስሜት ለመግባት ፈውስን ይጠቁማል፡፡

 

ከመጽሐፉ በጥቂቱ፡

በዚህች ምድር ላይ ስንኖር፣ አላህ ለእኛ አይታይም። ይህ ግን ለዐይነ-ሥጋችን ብቻ መሆኑ ይሰመርበት። በዐይነ ልቦናችን እርሱን ማየት እንችላለን። በነፍሶቻችንም እሱን ልናውቅ ይገባል። ግን፣ ግን ይህች ዓለም ፍፅምናን አልታደለችም። አንዳንድ ጊዜ ትጨልማለች፤የምትቀዘቅዝባቸው ጊዜያትም አሏት፤አንዳንዴም ፅልመትን ከርዝመት ያጣመሩ ሌሊቶች አይጠፏትም። ቁሩ፣ ማዕበሉም ሆነ ሕመሙ መኖሩ የግድ ነው። በዚህች ዓለም ስንኖር መድማት አይሻሬ ሕግ ነው። ከስሱነትና ተሰባሪነት፣ እንዲሁም ከጎዶሎነትና በአላህ ላይ ጥገኛ ከመሆን ስሜቶች ማምለጥ አይቻልም። ይህ ስሱነትም ነው ካልነበርንበት ምንምነት፥ ሕልውናን አድሎ ካስገኘን አምላክና አዳኛችን አላህ ጋር የሚያስተሳስረን ሲባጎ። …

 

ያንብቡት

ነጃሺ ማተሚያ  ቤት

የእውቀት ማዕድ!!!

************

 

 

 

 

 

 

 

SKU: M150 Category: