| Weight | 298 g |
|---|

የሙስሊም ስነምግባር
375.00 Br
አዘጋጅ፡ ሸኽ ሙሐመድ አል-ገዛሊ
ትርጉም፡ ኡስታዝ ዐብዱልዐዚዝ ሙሐመድ
ነጃሺ ማተሚያ ቤት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
ስለመጽሐፉ ይዘትና ማብራሪያ፡
ሰዎችን ወደ መልካም መንገድ መጥራት ብሎም መንገዳቸውን መቀየስ ታላቅ ተግባር ነው፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ዋናው ተግባራቸው የሰውን ልጅ ማነጽ ነበር፡፡ ለ13(አስራ ሶስት) ዓመታት በለፉበት በዚህ ተግባራቸው በቀላሉ ተዘርዝሮ የማይዘለቅ ትርፍ አካብተውበታል፡፡ ሙስሊሞችን በሥነ-ምግባር እንዲታነጹ አድርገዋል፡፡ ይህ መጽሐፍ ኢስላም ሥነ-ምግባራዊ አስተምህሮቱ ምን መምሰል እንዳለበት የሚያስረዳ ነው፡፡
ከመጽሐፉ በጥቂቱ፡
የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ጠንካራ ኢማን ምርጥ ሥነ-ምግባርን (አኽላቅን) እንደሚወልድ፥ የዘቀጠ ባህሪ የደካማ ኢማን ውጤት አልያም ኢማን ከነጭራሹ መጥፋቱን የሚያሳይ ምልክት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የተኮማተረ ፊት፣ ሰንካላ ሥነ-ምግባር፣ ያሻውን ነገር ለማንም ግድ ሳይኖረው የሚፈጽምን ሰው፥ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ በማለት ይገልጹታል፡-
“ኢማንና ይሉኝታ አንድ ላይ የተቆራኙ ናቸው፡፡ አንደኛው ከከሰመ ሌላኛውም ይከስማል::” (ጦበራኒና ሐኪም ዘግበውታል)
ጐረቤቶቹን የሚበጠብጥና የሚዘልፍ ሰው ሃይማኖቱ ከበድ ያለ ተግሳጽ ያደርስበታል፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)፥ “በአላህ እምላለሁ! አላመነም በአላህ እምላለሁ! አላመነም በአላህ እምላለሁ! አላመነም” አሉ፡፡ ሰዎችም “ማነው እርሱ (ያላመነው)?” ሲሉ ጠየቋቸው፡፡ እርሳቸውም “ያ በመጥፎ ሥነ-ምግባሩ የጎረቤቱን ደህንነት የረበሸ ነው” አሉ፡፡ (ቡኻሪ ዘግበውታል)
ያንብቡት
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
የእውቀት ማዕድ!!!
************




