
አርዓያ ቁ.2
335.00 Br
አዘጋጅ ፡ ኡስታዝ ሙሐመድ ዑመር አደም
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
ይዘት፡
መጽሐፉ በነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) ስብዕና ዙርያ በሁለት ክፍሎች ተቀናብሮ የተለያዩ ሥነምግባራቸውን በመዳሰስ ከምሳሌዎች ጋር ይዘረዝራል፡፡ ከራስ፣ ከፈጣሪያቸው፣ ከሰው ልጆች ጋር፣ ከቤተሰቦቻቸው፣ ከባልደረቦቻቸው፣ በዙርያቸው ካለው ዓለም ጋር የነበራቸው ግንኙነት ምን ይመስል እንደነበር በጥቂቱም ቢሆን ያሳየናል፡፡
ከመጽሐፉ፡
ሰው ውጫዊ ውበት እንዳለው ሁሉ ሥነ ምግባር የሚባል የውስጥ ውበትም አለው። ከዚህም የተነሳ ከገጽታ ውበት በላይ የውስጥ ውበቱ ሳቢና ማራኪ ይሆናል። ተፅዕኖውም ከፍተኛ ነው። የሥነ ምግባር ውበት የተግባቦትን ኃይል በእጅጉ ይጨምራል። በተለይም የሥነ ምግባር መሠረቶች የሆኑት እውነተኝነት፣ ታማኝነት፣ ታጋሽነት፣ ይቅር ባይነትና የመሳሰሉት ወሳኝነት አላቸው። ሰዎች ‘ይህ ሰው የሚለውን ነገር ልናዳምጠውና ልንታዘዘው የሚገባ ነውን?’ የሚል የውስጥ ጥያቄ አላቸው። የዚህን ጥያቄ መልስ የሚሰጠው ደግሞ ግለሰቡ ካለው እውቀት የበለጠ ሥነ ምግባሩ ነው። ከዚህም የተነሳ ሥነ ምግባር ከእውቀት በላይ ተቀባይነትና ታማኝነትን ያስገኛል። አልማወርዲ በተለይም ስድስት ባሕርያት ወሳኝነት እንዳላቸው ይናገራሉ። እነዚህ ባሕርያት ብልሕነት፣ ፈተናን የመቋቋም ብቃት፣ በሥጋዊ ነገር ልከኛ ጠባይ ማሳየት፣ ትህትና፣ ታጋሽነት እና ቃል አክባሪነት ናቸው። እነዚህ ባሕርያት ከፍተኛ መከበርን፣ ተቀባይነትንና መታመንን ይፈጥራሉ።›
ያንብቡት
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
የእውቀት ማዕድ!!!
************




