
ነፍሲያን ማረቅ
135.00 Br
አሳታሚ ነጃሺ ማተሚያ ቤት
አዘጋጅ ፡ ኢብን አል-ጀውዚ
ትርጉም ፡ ሱለይማን ጠይብ ሐምዛ
ስለመፅሃፉ ጥቂት ማብራሪያ
መጽሐፉ ነፍሲያን በማረቅ እና አጉል ፍላጎቶቿን በማገድብ ወደ ትልቅ ደረጃ ማድረስ ስለሚቻልበት ሁኔታ ይዳስሳል፡፡
ከመጽሐፉ ፡ አላህ ለሰው ልጆች የሚወስነውም ሆነ የሚያመላክተው ነገር ሁሉ ፋይዳው ለእነሱ ነው። አንድም እንደ የምግብ ፍላጎት ዓይነት ጠቃሚ ስሜቶች እንዲኖሯቸው አለዚያም እንደ ቁጣ ኃይል የመሣሠሉትን ክፋቶችን ለመቆጣጠር ነው። የምግብ ፍላጎት ወሰን ሲያልፍ ወደ ስግብግብነት ያመራል። በዚህ ምክንያትም ጎጂ ይሆናል። በተመሳሳይም የሰው ቁጣ ሚዛን ሲስት ጥፋት ማስከተሉ አይቀርም።
የዚህ መጽሐፍ ዋና ዓላማ የምጣኔን እና ትክክለኛነትን ሕግ በአእምሮ እና በልብ አውታሮች ውስጥ ማስረፅ፣ ማንበር እና ‹ሀዋእ› (ሥጋዊ ዝንባሌ) ጉዳት እንዳያስከትል መድፈቅ የሚቻልበትን መንገድ መጠቆም ነው። አለፍ ሲልም የምጣኔን እና ትክክለኛነትን ሕግ የሚቃወምን ሥጋዊ ዝንባሌ ፈውሶችን ያመላክታል።
መጽሐፉ በአጫጭር ሰላሳ ምዕራፎች የተከፋፈለ ነው::
ከመጽሐፉ በጥቂቱ፡
የስንፍና መድኃኒቱ ግብን ለማሳካት ብሎም መደናቀፍ ውድቀት ጸጸት እንዳይከሰት ለጥረት መነሳሳት ነው ፡፡ ጠንካራ ሰራተኛ ምንዳው ሲያገኝ ሰነፍ ሰው ላይ የሚከሰተውን ጸጸት የዳተኛ ትልቁ ቅጣት ነው፡፡
ያንብቡት
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
የእውቀት ማዕድ!!!
************




