| Weight | 204 g |
|---|

ምሶሶዎቹ
205.00 Br
አዘጋጅ ፡ ኡስታዝ አቡል አዕላ አልመውዱዲ
ትርጉም ፡ ሱለይማን ጦይብ
ስለመጽሐፉ ይዘትና ማብራሪያ፡
መጽሐፉ ‘Let us be Muslim’ የተሰኘው የአዘጋጁ ኹጥባዎች ስብስብ ነው። መጽሐፉ በዋናነት በኢስላም ማዕዘናት ጭብጥ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ስለ እምነት፣ እስልምና፣ ሶላት፣ ዘካ፣ ሐጅ እና ጂሃድ ተዳሶበታል፡፡ መጽሐፉ በሒንዱስታን ምድር ለነበሩ ሙስሊሞች የተዘጋጀ ሆኖ ከተሰናዳ በርካታ ዐሥርት ዓመታት ተቆጥሯል፡፡ ቢሆንም አሁንም ድረስ በሁሉም የዓለማችን ክፍል ለሚገኙ ሙስሊሞች ተገቢነቱ አልቀነሰም። በዚህ ምክንያት እስካሁን ቢያንስ በአስራ ሦስት የዓለማችን ቋንቋዎች ተተርጉሞ በርካታ አንባቢዎች እጅ ገብቷል። አዘጋጁ በበርካታ የሕትመት ውጤቶቻቸው ዓለማቀፍ ተቀባይነት ያላቸው ናቸው፡፡
ከመጽሐፉ በጥቂቱ፡
እውነተኛ ሙስሊም ለመሆን ዐቢይ ቅድመ ሁኔታ ኢስላምን ማወቅ ነው። እያንዳንዱ ሙስሊም የቁርኣንን አስተምህሮ ምንነት፣ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) የዘረጉትን ሥርዓት ባሕርይ፣ የኢስላምን ብያኔ እና ኢስላምን ከክሕደት የሚለዩትን ጉዳዮች ማወቅ ይገባዋል። ይህን የማያውቅ ሙስሊም ሊሆን አይችልም። ግና በሚያሳዝን መልኩ እነዚህን ጉዳዮች ለማወቅ አንጓጓም። ያጣነውን ሥጦታ ዋጋና ልክ አናውቅም። በመጀመሪያ የራሳችን ዲንን ባለማወቃችን ምን ያህል ውድ ነገር እያጣን መሆኑን መገንዘብ ይኖርብናል። የአላህ መጽሐፍ በእጃችን ነው፤ ሆኖም ምን ብዙዎቻችን እንደያዘ አናውቅም። ታዲያ ከዚህ የከፋ ምን ኪሣራ አለ? ወደ ኢስላም የምንገባበትን ‘ከሊማ’ ትርጉም እንኳን አናውቅም። ታዲያ ሙስሊም ከዚህ የሚልቅ ክሥረት ይገጥመዋል?
ያንብቡት
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
የእውቀት ማዕድ!!!
************




