| Weight | 120 g |
|---|

ሐያቱ ታቢዒዪን ክፍል ሁለት
165.00 Br
አዘጋጅ ፡ ዶ/ር ዐብዱረሕማን ረእፈት አልባሻ
ትርጉም ፡ አምባሳደር ኡስታዝ ሐሰን ታጁ
አሳታሚ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
ይዘት፡
ታቢዒዪኖች የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ባልደረቦችን ተከትለው የመጡ ከነርሱ ጋር የተገናኙና የኖሩ ትውልዶች ናቸው፡፡ ይህ መጽሐፍ በሁለት ቅጽ የተዘጋጀ ሲሆን የተለያዩ ታቢዒዮችን የሕይወት ታሪክ (ሐያቱ ታቢዒን) አጠር ባለ መልኩ ይዳስሳል፡፡ መጽሐፉን ያዘጋጁት ሐያቱ ሶሐባን ያዘጋጁት ዶ/ር ዐብዱራሕማን ረእፈት አልባሻ ናቸው፡፡ የታቢዒ ትውልዶች ዘመናቸውን ወርቃማ በማድረግ ዓለምን በበጐ ሥራዎቻቸውና በዕውቀታቸው ያደመቁ ነበሩ፡፡ ኢስላም በእስያ አህጉር ብቻ ተወስኖ ሳይቀር ከፀሐይ መውጪያ እስከ ፀሐይ መግቢያ እንዲስፋፋ ያላሰለሰ ጥረት አድርገዋል፡፡ የአባቶቻቸውን ዓላማ ክንዳቸውን እስኪንተራሱ ከግቡ አድርሰዋል፡፡ መጽሐፉ ይህንን ይነግረናል፡፡
ከመጽሐፉ በጥቂቱ፡
በቁጥር አንድ መጽሐፍ ዉስጥ የዐጧእ ኢብኑ አቢ ረባሕ፤ ዓሚር ኢብኑ ዐብዱላህ አት-ተሚሚ፣ ዑርወት ኢብኑ ዙበይር፣ ረቢዕ ኢብኑ ኹሠይም፣ ኢያስ ኢብኑ ሙዓዊያ ፣ ዑመር ዐብዱልዐዚዝ፣ ሐሰን አልበስሪ፣ ሹረይሕ አል-ቃዲ፣ ሙሐመድ ኢብኑ ሲሪን፣ ረቢዐቱ ረእይ፣ ረጃእ ኢብኑ ሐይወት፣ ሸዕቢ፣ ሰለመት ኢብኑ ዲናር፣ ሰዒብ ኢብኑ ሙሰየብ፣ ሙሐመድ ኢብኑ ዋሲዕ ታሪኮችን ያገኛሉ፡፡
ያንብቡት
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
የእውቀት ማዕድ!!!
************




