
ሐቢብ(ሀላልን ፍለጋ ቁ.2)
335.00 Br
አዘጋጅ፡ ኡስታዝ ሙሐመድ ዑመር አደም
አሳታሚ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
ስለመጽሐፉ ይዘትና ማብራሪያ
በነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) ስብዕና ዙርያ ያተኮረ መጽሐፍ ሲሆን በተለያዩ ክፍሎች ተቀናብሮ ያማረ ሥነ-ምግባራቸውን በመዳሰስ ከምሳሌዎች ጋር ይዘረዝራል፡፡ ከራስ፣ ከፈጣሪያቸው፣ ከሰው ልጆች ጋር፣ ከቤተሰቦቻቸው፣ ከባልደረቦቻቸው፣ በዙርያቸው ካለው ዓለም ጋር እና ከሌሎችም የነበራቸው ግንኙነትም እንዴት እንደነበር ይፈትሻል፡፡
ከመጽሐፉ በጥቂቱ:
ሰው ውጫዊ ውበት እንዳለው ሁሉ ሥነ ምግባር የሚባል የውስጥ ውበት አለው። ከዚህም የተነሳ ከገጽታ ውበት በላይ የውስጥ ውበቱ ሳቢና ማራኪ ይሆናል። ተጽእኖውም ከፍተኛ ነው። የሥነ ምግባር ውበት የተግባቦትን ኃይል በእጅጉ ይጨምራል። በተለይም የሥነ ምግባር መሠረቶች የሆኑት እውነተኛነት፣ ታማኝነት፣ ታጋሽነት፣ ይቅር ባይነትና የመሳሰሉት ወሳኝነት አላቸው። ሰዎች ‘ይህ ሰው የሚለውን ነገር ልናዳምጠውና ልንታዘዘው የሚገባ ነውን?’ የሚል የውስጥ ጥያቄ አላቸው። የዚህን ጥያቄ መልስ የሚሰጠው ደግሞ ግለሰቡ ካለው እውቀት የበለጠ ሥነ-ምግባሩ ነው። ከዚህም የተነሳ ሥነ ምግባር ከእውቀት በላይ ተቀባይነትና ታማኝነትን ያስገኛል። አልማወርዲ በተለይም ስድስት ባሕርያት ወሳኝነት እንዳላቸው ይናገራሉ። እነዚህ ባሕርያት ብልሕነት፣ ፈተናን የመቋቋም ብቃት፣ በሥጋዊ ነገር ልከኛ ጠባይ ማሳየት፣ ትህትና፣ ታጋሽነት እና ቃል አክባሪነት ናቸው። እነዚህ ባሕርያት ከፍተኛ መከበርን፣ ተቀባይነትንና መታመንን ይፈጥራሉ።›
ያንብቡት
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
የእውቀት ማዕድ!!!
************




