ፈውስና ዱዓእ

2.00 $

ማንኛዉም ሙስሊም በታመመ ጊዜ ሊታከምባቸው የሚገቡ ቁርኣንና ሐዲሥን መሠረት ያደረጉ ዱዓዎች አሉ፡፡ በዚህ መልኩ የሚደረግ ሕክምና ሩቅያ ይሠኛል፡፡ በዚህ መጽሐፍ የታመመን ሰው ለመፈወስ የምንጠቀምባቸው ዱዓዎችና ሌሎችም ተካተዋል፡፡ ይህ መጽሐፍ ሁለት ክፍሎችን አካቷል፡፡ የተለያዩ በሽታዎችን ለማከም የሚረዱ በቁርኣንና በሐዲስ የተወሱ የሕክምና ስልቶች የተካተቱበት አንደኛው ክፍል ሲሆን፣ ሁለተኛው ክፍል ደግሞ ከቁርኣንና ከሐዲስ የተውጣጡ ዱዓዎች የያዘ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ በድግምት፣ በሰው ዓይን፣ በጭንቀት፣ በቁስልና በመሰል ሕመሞች ለሚሰቃዩ ማድረግ ያለባቸውን የሚጠቁም ነው፡፡

አዘጋጅ ፡ ሰዒድ ኢብኑ ዐሊ ኢብኑ ወህፍ አል-ቀሕጣኒ
ትርጉም ፡ ኢድሪስ ሙሐመድ
የገጽ ብዛት ፡
የታተመበት ዓመት ፡
ከመጽሐፉ ፡ በቅዱስ ቁርኣንና በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ሐዲሥ በፀደቁ የመፈወሻ ስልቶች (ሩቃ) ፈውስን መሻት እጅግ ጠቃሚና የተሟላ ፈውስን የሚያስገኝ መሆኑ ቅንጣት አያጠራጥርም፡፡ ቁርኣን ለአመኑ ሰዎች መድህን ነዉና፡፡ ቁርኣን ለልቦናም ለአካልም፣ ለዚህችም ሆነ ለቀጣዩ ዓለም በሽታዎች ሁሉ ፈውስ ነው፡፡ ….

አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት