ጥያቄና መልስ

1.00 $

ከዚህ ቀደም በርካታ የጥያቄና መልስ መጽሐፎች በተለያየ መጠንና መልክ በተለያዩ አዘጋጆች ተዘጋጅተዋል፡፡ ይህች በሙሐመድ ሰዒድ የተዘጋጀችው አነስተኛ መጽሐፍም አጠር ባለና አዝናኝ በሆነ መልኩ የቀረቡ ጥያቄዎች ተካተውባታል፡፡ ጥያቄዎቹም ከዓለማዊ እስከ ሃይማኖታዊ ድረስ ያካተቱ ሲሆን፣ ከቀላል እስከ ከባድ ይዘት ያላቸውን በሦስት ደረጃ የተከፈሉ ናቸው፡፡ በተለይ ታዳጊ ልጆችና ለተማሪዎች ጥሩ መረጃዎችን ያገኙባታል ብለን እናምናለን፡፡
አዘጋጅ ፡ ሙሐመድ ሰዒድ
የገጽ ብዛት ፡ 148
የታተመበት ዓመት ፡ የካቲት 2011

ከመጽሐፉ ፡
1. የመጨረሻው የአላህ መልዕክተኛ ማን ይባላሉ?
2. አላህ ከሰው ልጆች ሁሉ ቅድሚያ የፈጠረው ማንን ነው?
3. የእስልምና ማዕዘናት ስንት ናቸው?
4. የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ሰሐቦች መጀመሪያ የተሰደዱባት አገር ማን ትባላለች?
5. በዓለም በብዛት ሙስሊሞች የሚኖሩባት ሀገር ማን ናት?

አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: