Weight | 82 g |
---|
ጥቂት የረመዳን ቀናት
$1.00
ጥቂት የረመዳን ቀናት
ዝግጅት፡ ዶ/ር መጅዲ ሒላሊ
ትርጉም፡ ዐብዱረዛቅ ነጋሽ
የገጽ ብዛት፡ 75
ስለ ታላቁ የረመዳን ወር ዝግጅት ይረዳ ዘንድ የተዘጋጀው ይህ መጽሐፍ በሦስት ምዕራፎች የተከፋፈለ ሲሆን እጅግ አጥሮ ግን ደግሞ መሠረታዊ የሚባሉ በረመዳን ለመጠቀም የሚያስችሉ ወሳኝ ምክሮችና ጥቆማዎችን አቅርቧል፡፡ በመጀመሪያው ምዕራፍ ላይ ከረመዳን ማትረፍ ያለብንን እንድናተርፍ የሚያደርጉ፤ ነፍስን የሚያነቃቁ ምልከታን የሚያሰፉ ርዕሰ ጉዳዮችን ያነሳል፡፡ አምልኮዊ ጉዳዮች ሲከናወኑ በልቦና ላይ ተጽዕኖ እንዲያመጡ፤ ለተግባር የቀረቡና ውስጥን የሚያነቃቁ መልእክቶችን በዝርዝር ይመክርበታል፡፡ በዚህ ታላቅ ወር ምንዳ ከማግኘት በላይ መገኘት ስላለባቸውም ከፍ ያሉ መንፈሳዊ ጉዳዮችም በመጽሐፉ ላይ ይቀርብበታል፡፡ በሁለተኛው ምዕራፍ ላይ ከረመዳን ማትረፍ ስላለብን ዋና ግቦችና ዓላማዎች አንጻር በረመዳን ውስጥ ስለሚገጥሙን የተለያዩ ችግሮች መውጫ መንገዶችን ይጠቁመናል፡፡ በዚህ ክቡር ወር ከአላህ ጋር እና ከሰዎች ጋር ሊኖረን የሚገባውንም ግንኙነት ሒደት በሚገባ ተተንትኗል፡፡ በመጨረሻውም ምዕራፍ እንዴት በዚህ ወር በመንፈስ መታደስ ይቻላል? በሚል ርዕስ በቁርጠኝነት ልንተገብራቸውና ልናተርፍባቸው የሚገቡ ተግባራትን ይቀርብበታል፡፡ አላህ አንብበው ከሚጠቀሙት ባሮች መካከል ያድርገን፡፡