Weight | 60 g |
---|
ጣፋጭ ታሪኮች ለልጆች ቁ. 2
$1.00
መጽሐፉ በአራት ክፍሎች (ቁ 1-4) የተዘጋጀ ሲሆን ከ100 የሥነምግባርና ሞራላዊ ታሪኮች ተካተዉበታል፡፡ በአራት ቅጾች የተዘጋጀው ይህ መጽሐፍ ለሀገራችን የልጆች ጠቃሚ በሆነ መልኩ የተሰናዳ ነው፡፡ የተለያዩ ታሪኮቹ የማስተማር የማዝናናት የማሳወቅ ሚናቸው ከፍተኛ ነው፡፡ በሰዎች ደካማና ጠንካራ ባህሪ ላይ የተመሠረቱ በጥቅም ፈላጊዎችና መንፈሳዊ ሕይወት ፈላጊዎች ላይ የተመሰረቱ በርካታ ታሪኮችን ለልጆች ለአዋቂዎችም ጭምር የሚያስነብብ መጽሐፍ ነው፡፡
መጽሐፉ ሞራልን፣ መልካም ሥነምግባርንና ኢስላማዊ በጐ አስተሳሰብን ልጆች እንዲላበሱ የሚረዳ ነው፡፡ ሙስሊማዊ ፍቅርንና መደጋገፍን የወላጅ ሐቆችን፣ የኢማን ደረጃን፣ እውነተኛነትን፣ ለጋስነትን፣ የደስታ ምስጢሮችን፣ የክፋት፣ የተንኮልና የስስታምነት መጨረሻን ማራኪ በሆነ አቀራረብ ለልጆች ይተርካል፡፡ መጽሐፉ ልጆችን ብቻ ሳይሆን ለአዋቂዎችም የሚጠቅም ትምህርት አለው፡፡
አዘጋጅ ፡ አክረሙላህ ሰዒድ
ትርጉም ፡ አወድ ዐብዱሶቡር
የገጽ ብዛት ፡ ቁ፡ 1- 52 ገጽ ቁ፡2- 56 ገጽ ቁ፡3- 48 ገጽ
የታተመበት ዓመት ፡ ነሐሴ 2002
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት