ገንዘብ ቅጽ 1

6.00 $

እስልምና ሚዛናዊ ሃይማኖት ነው፡፡ ለመንፈሳዊም ሆነ ዓለማዊ፣ ለሥጋም ይሁን ለነፍስ ፍላጎት ትኩረት ይሰጡ ዘንድ ተከታዮቹን ያዛል፡፡ ወደ አንዱ ከልክ ባለፈ መልኩ በማጋደል ሌላኛዉን ሕይወታቸዉን እንዳይጎዱ ይመክራል፡፡ አማኞች በዚህም ሆነ በመጨረሻው ዓለም ይሳካላቸው ዘንድ አስፈላጊዉን ነገር ሁሉ ይጠቁማል፡፡ ገንዘብ በሕይወታችን ዉስጥ እጅግ አስፈላጊ ከሆኑ ነገሮች መካከል አንዱ ነው፡፡ ስለሆነም እስልምና ትኩረት ችሮታል፡፡ ለአሰባሰቡም ሆነ ለአያያዙ፣ ለአዋዋሉም ቸልተኞች እንዳይሆንና ሸሪዓው በሚፈቅደው መልኩ እንድንጠቀምበት አሳስቧል፡፡ ይህ መጽሐፍ ስለ ገንዘብ በእስልምና ዉስጥ ስላለው እይታ፣ ስለ ገንዘብ ምንነትና አስፈላጊነት፣ ስለ አያያዙ፣ ለገንዘብ ምንጭ ስለመጠንቀቅና ስለ ሌሎችም በርካታ ተያያዥ ጉዳዮች ያወሳል፡፡ አዘጋጁ መጽሐፉን ለማዳበር በርከት ያሉ መጽሐፎችንና የተለያዩ መረጃዎችን በምንጭነት ተጠቅሟል፡፡
አዘጋጅ ፡ ሙሐመድ ዑመር አደም
የገጽ ብዛት፡ 240
የታተመበት ዓመት ፡ 2012
ከመጽሐፉ ፡ ገንዘብ የሕይወት ግቦቻችንን ለማሳካት ይጠቅመናል እንጅ የመኖር ግባችን ግን አይደለም። የሰው ልጅ አይነተኛው ግቡ እዚህ ሳይሆን እዚያ ነው። ይህንን እውነታ መለኮታዊ መመሪያዎች አጽንኦት ሰጥተው አስተምረውታል። ከዚህም የተነሳ ገንዘብ አላህ ዘንድ የማንንም ሰው ትልቅነት ወይም ትንሽነት አያመለክትም። ይህን የሚያሳየው አላህ ለአማኙም ሆነ ለካህዲው ለሚወደውም ሆነ ለሚጠላው ሃብትን የሰጠ መሆኑ ነው። ለምሳሌ ለነብዩላሂ ሱለይማን ንግሥናንና ሃብትን ሰጥቷል። በተመሳሳይ ሁኔታም ለፊርዖንም ንግስናንና ሃብትን ሰጥቷል። በሁለቱ ሰዎች መካከል ደግሞ ሰፊ ልዩነት አለ።
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category:

Additional information

Weight 214 g