ጀነት መግባት ትፈልጋለህን?

$4.00

ጀነት መግባት የማይፈልግ ይኖር ይሆን? … በርግጥ ሊኖር አይችልም፡፡ ይህ መጽሐፍ ከተለያዩ ምንጮች ተተርጉሞ የተቀናበረው በሁለት ፀሐፊዎች የተዘጋጀ ሲሆን የመጀመርያው ክፍል ስለ ጀነት ምንነት፣ ስለ መክፈቻ ቁልፎቿ፣ ጀነት ለመግባት ምክንያት ስለሆኑ ነገሮች በዝርዝር የሚዳስስ ነው፡፡ ሁለተኛው ክፍል ደግሞ ስለ ንፁህ ቀልብ አስፈላጊነት ያወሳል፡፡ ከሥራም በበለጠ ንፁህ ለጀነት መግባት ምክንያት እንደሆነ ይዘረዝራል፡፡ በዚሁ ዙርያ ቀልባችንን ሊያጠሩልን የሚችሉ ዉብ ምሳሌዎችንና የቀደምት ደጋግ ፈለጎችን እያነሳ ያጓጋናል፡፡
ትርጉምና ቅንብር ፡ ዐብዱልፈታሕ ሙሐመድ እና ሙሐመድ ሰዒድ
የገጽ ብዛት ፡ 124
የታተመበት ዓመት ፡ የካቲት 2006
ከመጽሐፉ ፡
በዒባዳውና ከዚህች ዓለም ጥቅም ግድየለሽ በመሆን የሚታወቀውን ሳሊም ኢብኑ ዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር/ የኸሊፋ ዑመር ኢብኑልኻጧብ የልጅ ልጅ ነው፡፡/ የሀጅ ሥርዓት ለመፈፀም ወደ ሚና ሄደ፡፡ አላህ ሆይ! ያንን ምድር ሣንረግጥ አትግደለን!፡፡ ሚና በሀጅ ወቅት ሰው ስለሚበዛበት መጨናነቁ ግፍያውና ትርምሱ የታወቀ ነው፡፡ ትኩረቱን ሐጁ ላይ ያደረገው ዐብደላህ ሣይታወቀው የሆነ ሰው ገፍቶ ኖሯል፡፡ ይኸው ሰውዬ ወደዚህ የወቅቱ ታዋቂና ታላቅ ታቢዒ ወደነበረው ሣሊም ኢብኑ ዐብዱላህ ዘወር በማለት ‹መጥፎ ሰው ትመስለኛለህ፡፡› በማለት ወረፈው፡፡ ሳሊም ለዚህ የሰጠው ምላሽ አጭር ነበር ‹ ካንተ በቀር ያወቀኝ የለም፡፡›

አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: