ድህነት እና ኢስላማዊ መፍትሄው

6.00 $

ኢስላም ለምድራዊ ችግሮች ሁሉ መፍትሄ ያለው ሃይማኖት ነው፡፡ ድህነት መንስኤው ምንም ይሁን ምን ትልቅ ማኅበራዊ ችግር ነው፡፡ መጽሐፉ የሚያተኩረው የኢስላማዊው ኢኮኖሚያዊ ሥርዓት አንድ ክፍል በሆነው በድህነት እና ሕክምናው፣ በድሆች መብት አጠባበቅ፣ መሠረታዊ ፍላጐታቸውን በማሟላት፣ ክብራቸውን በመንከባከብ ላይ ነው፡፡ መጽሐፉ ኢስላም በድህነት ዙርያ ስላስቀመጠው መፍትሄ ለተማሪዎች፣ ለማኅበረሰብ ችግር ተመራማሪዎችና ለሌሎችም ጥሩ ማጣቀሻ ሊሆን የሚችል ነው፡፡  በኢስላማዊ ሸሪዓ ጥላ ሥር ይህ የድህነት ህክምና እንዴት ሊከናወን እንደሚችል ያሳየናል፡፡
አዘጋጅ ፡   ፕ/ር ኢማም ዩሱፍ አልቀርዷዊ
ትርጉም ፡ ሐሰን ታጁ
የገጽ ብዛት፡  200
የታተመበት ዓመት ፡ ነሐሴ 2001
ከመጽሐፉ ፡ ኢስላም ድህነትን መፍትሔ የሚሻ ችግር አድርጎ ያየዋል። ሊከላከሉት እና ሊያክሙት የሚገባ አደገኛ በሽታ እንደሆነም ያምናል። ድህነት ሊታከም የሚችል በሽታ መሆኑንም ይቀበላል። ድህነትን መዋጋት የአምላክን ፈቃድ መዋጋት አይደለም። ድህነትን የሚያወድሱ፣ እርሱን እንደ በጎ ነገር፣ ሀብትን እንደመከራና እንደ አምላክ ቅጣት አድርገው የሚቆጥሩ እይታዎችን ይቃወማል። ድህነት ሊለወጥ የማይችል የአምላክ ፈቃድ፣ ሸሽተው የማያመልጡት እና የማይገሰስ የአምላክ ፍርድ፣ በጸጋ ከመቀበል ውጭ ሌላ ሕክምና የሌለው በሽታ አድርጎ የሚያየውን እይታም ክፉኛ ይነቅፋል፡፡ ድህነትን ለመቅረፍ በግለሰቦች በጎ ፈቀድ የሚሰጥን ምጽዋት ብቻ እንደ ስልት መጠቀምንም አይቀበልም፡፡
አሳታሚ ፡ ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Category: